1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ737 ማክስ አውሮኘላን አደጋ  ኃላፊነት

ረቡዕ፣ ኅዳር 8 2014

በኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ አውሮኘላን አደጋ ጋር በተያያዘ ቦይንግ ኩባንያ ኃላፊነት መውሰዱ በፍትሕ ሂደቱ ትልቅ ርምጃ መሆኑን ዶይቸ ቨለ ያነጋገራቸው የተጎጂ ቤተሰቦች ጠበቃ ገለፁ።

https://p.dw.com/p/437As
USA Anwalt Shakespear Feyissa
ምስል Tariku Tessema

ከየተጎጂ ቤተሰቦች ጠበቃ ጋር የተደረገ ቃለመጠይቅ

በኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ አውሮኘላን አደጋ ጋር በተያያዘ ቦይንግ ኩባንያ ኃላፊነት መውሰዱ በፍትሕ ሂደቱ ትልቅ ርምጃ መሆኑን ዶይቸ ቨለ ያነጋገራቸው የተጎጂ ቤተሰቦች ጠበቃ ገለፁ። በአደጋው የተጎዱ የተወሰኑ ቤተሰቦችን ወክለው ጥብቅና የቆሙት አቶ ሼክስፒር ፈይሳ እንዳሉት ቦይንግ ለደረሰው አደጋ ጥፋተኛነቱን የተቀበለው ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ የቆየ ሂደት በኃላ ነው። በምላሹም የተጎጂ ቤተሰቦች ኩባንያው ላደረሰው ጉዳት በፍርድ ቤት የመቀጣጫ ቅጣት እንዲጣልበት እንደማይጠይቁ የሕግ ባለሞያው አመልክተዋል። ከሕግ ባለሞያው ጋር ቆይታ ያደረገው ዘጋቢያችን ዝርዝሩን አድርሶናል። 

ታሪኩ ኃይሉ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሰ