1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ ዝግጅትና ድባብ በጋዜጠኞች ዕይታ

እሑድ፣ ሰኔ 13 2013

ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ በኢትዮጵያ ሊካሄድ የሁለት ቀናት ዕድሜ ብቻ ቀርቶታል። ምርጫው ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ከተካሄዱ ምርጫዎች ውጤታቸው የታሰበውን አምጥቷል አላመጣም እንዳለ ሆኖ በብዙ መልኩ ይለያል።

https://p.dw.com/p/3vDNf
Äthiopien Wahlkampf in Addis Abeba
ምስል Negash Mohammed/DW

እንወያይ ሰኔ 13 ቀን 2013

ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ በኢትዮጵያ ሊካሄድ የሁለት ቀናት ዕድሜ ብቻ ቀርቶታል። ምርጫው ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ከተካሄዱ ምርጫዎች ውጤታቸው የታሰበውን አምጥቷል አላመጣም እንዳለ ሆኖ በብዙ መልኩ ይለያል። ቀዳሚው በተደጋጋሚ ሊካሄድ ከታሰበለት ጊዜ በተለያዩ ምክንያቶች መገፋቱ ሲሆን፤ ምርጫውን የሚያስፈጽመው የምርጫ ቦርድ አወቃቀርም ትኩረትን አሰጥቶታል። በዚያም ላይ በጸጥታና ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች ምርጫው በሁለት የተለያዩ ቀናት መካሄዱም የተለየ ገጽታው ነው። በእስር ላይ የሚገኙ እጩ ተፎካካሪዎችም በዚህ ምርጫ መሳተፋቸው ይለየዋል። በዚህ ምርጫ ድምጹን ለመስጠት ከ 37 ሚሊየን በላይ ዜና መመዝገቡን የምርጫ ቦርድ አሳውቋል። ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ,ም በኢትዮጵያ የሚካሄደው የስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ዝግጅት፤ የሕዝቡ ስሜት እንዴት ይታያል? 

 ሸዋዬ ለገሠ 

አዜብ ታደሰ