1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ2014 አዲስ አመት ልዩ ዝግጅት

ቅዳሜ፣ መስከረም 1 2014

በበዓል ልዩ ዝግጅታችን ከአዲስ አበባ፣ ከመቐለ፣ ከድሬዳዋ እና ከሐዋሳ የተላኩ ዘገባዎች ተካተዋል። በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በግጭቶ ሳቢያ የተፈናቀሉ ዜጎችን የበዓል አከባበር የሚመለከቱ ዘገባዎችም ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/40Cfo
Young Flower Adey Abeba Blumen Äthiopien
ምስል Yohannes Geberegziabeher

የአዲስ አመት አከባበር ውጊያ በሚደረግበት ጊዜ-ሰለሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ

የዘንድሮው አዲስ አመት እንደወትሮው አይደለም። ላለፉት አመታት ሲብላላ የቆየው ፖለቲካዊ ቀውስ በኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ባለፈው ጥቅምት ውጊያ ቀስቅሶ አገሪቱን ለአዲስ ግን ደግሞ ብርቱ ቀውስ ዳርጓታል። ውጊያን ለሚያውቁ፣ በጦርነት አውድማ ለተሰለፉ ግን አዲስ አመት ለዛ የለውም፤ ሐዘን ይጫነዋል።

በዛሬው የበዓል ልዩ መሰናዶ የበዓል አከባበሩን የሚዳስሱ ዘገባዎች ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ተጠናቅረዋል። የአዲስ አበባው ሰለሞን ሙጬ የቀድሞ ወታደር አግኝቶ በዓል እንዴት እያከበሩ ነው? ሲል ጠይቋል። መልሳቸው ኢትዮጵያ የተጫናትን ስሜት ያንጸባርቃል።

በትግራይ የተቀሰቀሰው እና ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች የተዛመተው ውጊያ እና ውጊያውን የተከተለው ቀውስ ከተጫናቸው የኢትዮጵያ ከተሞች አንዷ መቐለ ነች። በከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ ያለውን ስሜት ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ ጠይቋል። ዓለምነው መኮንን የተፈናቀሉ ዜጎችን የበዓል ውሎ የተመለከተ ዘገባ ሲያጠናቅር ነጋሳ ደሳለኝ ከአሶሳ ለተፈናቃዮች የበዓል መዋያ የሰጡ የቡለን ወረዳ ወጣቶችን አነጋግሯል። መሳይ ተክሉ ከድሬዳዋ፤ ሸዋንግዛው ወጋየሁ ከሐዋሳ ለተቸገሩ ዜጎች የተደረጉ የበዓል ዕገዛዎች የተመለከቱ ዘገባዎች አሏቸው።

እንዲህ በዓል ሲከበር ኢትዮጵያውያን እንደየአቅማቸው ለመሸመት ወደ ገበያ ያቀናሉ። ለመሆኑ የአዲስ አመት ገበያ እንዴት ውሎ ይሆን? የዶይቼ ቬለው ስዩም ጌቱ ቅቤ፣ ዶሮ እና በግ ወደሚሸጥበት የዋጋ ውድነት ዜጎችን ወደሚያማርርበት ገበያ ብቅ ብሎ ነበር።

ሁሉንም ዘገባዎች መስፈንጠሪያዎቹን በመጫን እንዲያደምጡ እንጋብዛለን። 

ሰለሞን ሙጬ

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ዓለምነው መኮንን

ነጋሳ ደሳለኝ

መሳይ ተክሉ

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ስዩም ጌቱ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ ዘገባዎች አሳይ