1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ2014 ስንብት እና የአዲስ ዓመት ምኞት

ቅዳሜ፣ ጳጉሜን 5 2014

የመቐለው ወጣት 2014ን "የተወሳሰበ እና አስጨናቂ ዓመት" ይለዋል። የጉጂ አባገዳ ጂሎ ማንኦ "የዓመቱ የመከራው ጅራፍ ያልገረፈው ይኖራልም አንል" በማለት ይናገራሉ። የድሬዳዋ፣ ሐረር እና ጅግጅጋ ነዋሪዎችም ቢሆኑ ዓመቱን በበጎ አያነሱትም። 2014 ሲሸኝ በኢትዮጵያውያን የአዲስ ዓመት ምኞት የሰላም መሻት ልቆ ይሰማል

https://p.dw.com/p/4GfSc
Young Flower Adey Abeba Blumen Äthiopien
ምስል Yohannes Geberegziabeher

የመቐለ ነዋሪዎች የ2014 አስተያየት እና የ2015 ምኞት

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰበብ በትግራይ ክልል የተቋረጡ መሠረታዊ አገልግሎቶች ወነበሩበት አልተመለሱም። ወጣቶች ትምህርት እና ሥራቸውን አቋርጠው ተዋጊ ሆነዋል።ውትድርና ላልገቡትም ቢሆን ሕይወት ቀላል አልነበረም። የዶይቼ ቬለው ሚሊዮን ኃይለስላሴ ያነጋገረው ወጣት 201ትን "የኪሳራ ዓመት" ሲል ይገልጸዋል። ከመቐለ ነዋሪዎች የአዲስ ዓመት ምኞት የሰላም መሻት ልቆ ይሰማል።

በድሬደዋ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩት አቶ አለማየሁ 2014 "ህዝባችን በሰላም እጦት እና ኑሮ ውድነት የተፈተነበት" መሆኑን ያነሳሉ።  አቶ አለማየሁ "መጪው አዲስ አመት የኑሮ ውድነቱም ተስተካክሎ ፣ ያጣነው እና የናፈቀን ሰላም መቶ ህዝባችን ፍቅር በፍቅር የሚሆንበት ይመስለኛል" ብለዋል።

"2014 ዓ.ም እንደ ህዝብ የተፈትንበት ነው የሚሉት አቶ ቢንያም መጪው ጊዜ ይሄ ሁሉ የሚሻሻልበት እንደሚሆን ምኞት አለኝ ሲሉ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

የሀረር ከተማ ነዋሪው አቶ ኢማጅ በበኩላቸው በዓመቱ የነበሩ እውነታዎችን "ከትውልድ ጥሩ ታሪክ ብዬ አልወስድም ፤ በዓዲሱ ዓመት ይሄ ሁሉ ዳግም እንዳይመለስ ምኞታችን ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

የጅግጅጋ ነዋሪው አቶ ደረጀ "2014 የመጨረሻ የኢትዮጵያ አበሳ የሚወጣበት ዓመት ፤ የኢትዮጵያውያ ህዝብ ብዙ ትምህርቶች የሚማርበት ነው" ሲሉ አስተያየታቸውን ሰተዋል።

ፖለቲከኛ ሙላቱ ገመቹ በዓመቱ የሆነውን በቅርበት ስከታተሉት ነበርና ግጭት መፈናቀል ባህል የሆነበትን ዓመት እንዲህ አስታወሱት፡፡ “ዓመቱ በኦሮሚያ እምብዛም ትኩረት የተነፈገው፤ ነገር ግን አስከፊ እልቂትና መፈናቀል ብሎም የሃብት ውድመት የተስተናገደበት የስቃይ ዘመን” ብለውታል አቶ ሙላቱ፡፡

የዶይቼ ቬለዎቹ ሚሊዮን ኃይለስላሴ፣ መሳይ ተክሉ እና ስዩም ጌቱ ያጠናቀሯቸውን ዘገባዎች የድምጽ ማዕቀፎቹን በመጫን ያድምጡ።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

መሳይ ተክሉ

ስዩም ጌቱ

እሸቴ በቀለ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ