1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ2013 ግንቦት ወር የምርጫ ዝግጅት

እሑድ፣ የካቲት 14 2013

በየአምስት ዓመቱ የኢትዮጵያ የምታካሂደው ምርጫ ባለፈው ዓመት ኮቪድ 19 እንቅፋት ሆኖ በመገፋቱ በያዝነው ዓመት ግንቦት ወር ሊካሄድ ቀን ተቆርጦለታል።

https://p.dw.com/p/3pcVR
Karte Äthiopien englisch

እንወያይ የካቲት 14 ቀን 2013

በኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት የኮሮና ተሐዋሲ ወረርሽኝ ያደናቀፈውን ምርጫ ዘንድሮ ለማካሄድ ሦስት ወራት ገደማ ቀርተዋል። በምርጫው የሚሳተፉ ጥቂት የማይባሉ ፓርቲዎች የሚለዩበትን አርማ መርጠው፣ እጩዎችንም እያስመዝገቡ ለምርጫ ቅስቀሳዎች መንቀሳቀስ ጀምረዋል። በአንጻሩ እጩዎቻችን እና አባላቶቻችን ታስረዋል፣ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ጽሕፈት ቤቶችን ተዘግተዋል፤ በዚህ ሁኔታ በምርጫው እንዳንሳተፍ እየተገፋን ነው የሚሉም አሉ። ገዢው ፓርቲ በበኩሉ ከዚህ ቀደሙ የተሻለና የተለየ ምርጫ እንዲካሄድ የበኩሉን እያደረገ መሆኑን ይናገራል። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ