የ2011 ረቂቅ በጀት ፀደቀ
ዓርብ፣ ሰኔ 29 2010ማስታወቂያ
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ዛሬ በምክር ቤት ባደረጉት ንግግር በየሰበብ አስባቡ በየቦታዉ የሚታየዉ ግጭት አስመልክቶም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እንደግብርናዉ ሁሉ የትምህርቱም ዘርፍ ትኩረት ሊሰጠዉ እንደሚገባ ገልፀዋል። በሃገሪቱ የትምህርት ጥራት ችግርን ለመቅረፍ «ፍኖተ ካርታ» እየተጠናቀቀ መሆኑንና በቅርቡ ለዉይይት ቀርቦ ስራ ላይ እንደሚዉል ገልፀዋል። ኢትዮጵያ ሰላም እየሆነች ከሆነ ከዉጭ እናግዝ የሚል ብዙ ጥያቄ ይቀርብልናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስር ዶር አብይ አሕመድ ፤ በዉጭ ሃገራትን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በተቻለ መጠን የሚልኩትን ገንዘብ በባንክ በኩል እንዲያደርጉም ይቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የበጀት ዓመት ሳይሆን የቅድመ ድልድልን በሚመለከት በቀረበላቸዉ ጥያቄ መሰረት ማስረዳታቸዉን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ በዘገባዉ ገልፆልናል።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ