የ10,000 በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተመረቁ
ቅዳሜ፣ የካቲት 27 2013ማስታወቂያ
የ10,000 በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተመረቁ
በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ዮንቨርስቲዎች የተለያዩ ስልጠናዎችን የወሰዱ 10 000 የበጎ ፍቃደኛ ወጣቶችን ዛሬ የኢትዮጵያ የሰላም ሚኒስቴር አስመርቋል። ለስልጠናው ከ 100 ሺ በላይ ወጣቶች አመልክተው እንደነበረ የሰላም ሚኒስትሯ ተናግረዋል። በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ባሰሙት ንግግር «የመከላከያ ሰራዊቱ እና የፌደራል ፖሊስ ብዙ ወጣቶች እንዲቀላቀሉት ይፈልጋል።ይህም ከቅርብ እና ከሩቅ ብዙ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚፈልጉ ኃይሎች ስላሰፈሰፉ ነው ብለዋል። በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኘው የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ዮሀንስ ገብረእግዚያብሔር ተመራቂ ወጣቶችም አነጋግሮ ተከታዮን ዘገባ ልኮልናል።
ዮሀንስ ገብረእግዚያብሔር
ልደት አበበ