1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ባለቴኳንዶዎቹ እንስቶች

ማክሰኞ፣ ሰኔ 1 2013

ከፍተኛ አካላዊ አንቅስቃሴ በሚጠይቀው የቴኳንዶ ስፓርት ኢትዮጵያ ውስጥ ሴቶች ሲሳተፉ ማየት ብዙም የተለመደ ላይሆን ይችላል ። በርካቶች "ትሰባበራላችሁ፣ ይቅርባችሁ" ይሉን ነበር የሚሉት መቅደስ እዮብ እና በረከት በቀለ ወደ ስፖርቱ ከገቡ በኋላ ቴኳንዶን ከጠበቁት በላይ አስደሳች ሆኖ እንዳገኙት ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/3uapS

መቅደስ በቴኳንዶ አራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ሰማያዊ ቀበቶ አላት። በረከት ደግሞ ገና ጀማሪ ናት። የወደፊት ህልሟ ጥቁር ቀበቶ መያዝ ነው።  የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሊሻን ዳኜ ታዳጊዎቹ ወደሚሰለጥኑበት በሐዋሳ ከተማ የሚገኘው የወጣቶች ማዕከል በመሄድ አነጋግራቸዋለች። 

ዘገባ: ሊሻን ዳኜ
ቪዲዮ: ሸዋንግዛው ወጋየሁ