ዕርቅ በኢትዮጵያ
ሐሙስ፣ የካቲት 18 2013ማስታወቂያ
ኢትዮጵያን የሚያብጠዉን ፖለቲካዊ፣ ጎሳዊ፣ ኃይማኖታዊና ማሕበራዊ ቀዉስን ለመፍታት ባሕላዊዉና እምነታዊዉ የግጭት አፈታት ስልት የተሻለ ዉጤት ማሳየቱ ተነገረ።የኢትዮጵያ የሠላም ሚንስቴር «ዕርቅ በኢትዮጵያ» በሚል ርዕሥ ዛሬ ባዘጋጀዉ ዉይይት ላይ የተካፈሉ ባለሙያዎችና ሽማግሌዎች እንዳሉት ግጭትና ቀዉሶችን ለማስወገድ መንግሥት ከወሰዳቸዉ ርምጃዎች ይልቅ ልማዳዊዉ የግጭት አፈታት የከፋ ጥፋት እንዳይደርስ ረድቷል።የዉይይቱ ተካፋዮች በተለይ የጋሞ ሕዝብን የዕርቅ ሥርዓት ትኩረት ሰጥተዉ ተነጋግረዉበታል።
ሠለሞን ሙጪ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ