1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓለም አቀፍ የስልክ ጥሪዎች ችግር በኢትዮጵያ

ማክሰኞ፣ መስከረም 19 2013

ኢትዮ ቴሌኮም ዓለም አቀፍ ጥሪዎች ላይ ችግር እንደተከሰተ እንደሚያውቅ ገለጠ። ችግሩ መከሰቱን እንደሚያውቅ የተናገረው መሥሪያ ቤቱ በዛሬው ዕለት እንደሚፈታ ገልጿል። ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ ዓለም አቀፍ የስልክ ጥሪዎች ተደጋጋሚ ችግር ይስተዋልባቸዋል።

https://p.dw.com/p/3jAgN
Äthiopien Addis Abeba | Ethio Telecom building
ምስል DW/H. Melesse

ኢትዮ ቴሌኮም ችግሩ መኖሩን ያውቃል

ኢትዮ ቴሌኮም ዓለም አቀፍ ጥሪዎች ላይ ችግር እንደተከሰተ እንደሚያውቅ ገለጠ። ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ ዓለም አቀፍ የስልክ ጥሪዎች ተደጋጋሚ ችግር ይስተዋልባቸዋል። ሰሞኑን ዛሬን ጨምሮ ማለት ነው ለአብነት ያኽል ከዚህ ከጀርመን ከቦን ስቱዲዮዋችን ወደ ኢትዮጵያ የስልክ ጥሪ ማድረግ አስቸግሮናል። በጣልያንና ጀርመን መካከል የሚገኝ የስልክ መስመር ማገናኛ ገመድ በገጠመው የጥራት መጓደል ችግር ከአውሮጳ፣ በተለይም ከጀርመን ወደ ኢትዮጵያ የሚደረግ ዓለም አቀፍ የስልክ ጥሪ እክል እንደገጠመው ኢትዮ ቴሌኮም ዐስታውቊል። ችግሩ መከሰቱን እንደሚያውቅ የተናገረው መሥሪያ ቤቱ በዛሬው ዕለት እንደሚፈታ ገልጿል። ኩባንያው ከሀያ ሰባት ዓለም አቀፍ የስልክ ኦፕሬተሮች ጋር እንደሚሠራም ዐስታውቋል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰለሞን ሙቼ ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅሮልናል። 

ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶትስ ስለሺ
ኂሩት መለሰ