1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓለም አቀፉ የካቶሊካዉያን ጳጳሳት ጉባዔ

ሰኞ፣ የካቲት 18 2011

ጣልያን ቫቲካን ዉስጥ ለአራት ቀናት የዘለቀዉ ዓለም አቀፍ የካቶሊካዉያን ጳጳሳት ጉባዔ በቤተ-ክርስቲያኒቱ ዉስጥ ሕጻናት ላይ የሚፈፀመዉን የወሲብ ጥቃትና ትንኮሳ ወንጀልን ለመዋጋትና ወንጀለኛ የተባሉት ቄሶች ላይ ተገቢዉ ርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ በመግለፅ ተጠናቀቀ።

https://p.dw.com/p/3E3jk
Vatikan-Missbrauchskonferenz Papst Franziskus Messe
ምስል Reuters/CTV

ጉባዔዉ የወሲብ ጥቃትና ትንኮሳን በመታገል ላይ ትኩረት ሰጥቷል

ጉባዔዉ በተለያዩ የዓለም ሃገራት ዉስጥ በሚገኙ የካቶሊካዊት አብያተ ክርስትያናት ዉስጥ በልጆች እና በአዋቂዎች ላይ የተፈፀሙና የሚፈፀሙ የወሲብ ጥቃትና ትንኮሳን በግልጽ ለማዉጣትና ለመግታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ተወያይቷል።  ትናንት ያበቃዉን የቫቲካኑን ጉባዔ የመሩት የካቶሊካዊት ቤተ-ክርስትያን ርዕሰ ሊቃነ- ጳጳሳት ፍራንሲስ በበኩላቸዉ ስለ ችግሩ በግልፅ መወያየት እንዲሁም በግልፅ ማዉጣት እንዳለበት ተናግረዋል። በሌላ በኩል ጀርመንን ወክለዉ በጉባዔዉ የተሳተፉት የሙኒክና የፍራይዚንግ ጳጳስ ካርዲናል ራይንሃልድ ማርክስ ቫቲካን የወሲብ ትንኮሳ የፈፀሙ ግለሰቦችን ደብቃ ይዛለች ሲሉ ወቅሰዋል። ከ190 በላይ ጳጳሳት በተሳተፉበት በቫቲካኑ ጉባዔ ላይ  የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስትያንን ወክለዉ የጅማና ቦንጋ አገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ገብረመድሕን የተገኙ ሲሆን፤ የኤርትራ ካቶሊካዊ ቤተ-ክርስትያንን ወክለዉ ደግም የባሬንቱ አገረ ስብከት ጳጳስ ቶማስ ኦስማን ተገኝተዋል።  

Vatikan-Missbrauchskonferenz Papst Franziskus
ምስል REUTERS


ተኽለ እዝጊ ገብረየሱስ 


አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ