1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጥሪ

ዓርብ፣ ሐምሌ 30 2013

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዓለም አቁፉ ማኅበረሰብ በሺህዎች የሚቆጠሩ ንፁኃን ዜጎች ለጥቃትና ጉዳት ከመዳረጋቸው በፊት ፈጥኖ ሊደርስ ይገባል ሲል ጥሪ አቅርቧል። አሁን ይደረጋል ያለው ተገቢ ያልሆነ ጣልቃ ገብነት ሊቆም እንደሚገባም አስገንዝቧል።ኢትዮጵያ የገጠማትን ችግር ከራስ ብሔራዊ ጥቅም ብቻ መቃኘት ኢሰብዓዊነት ነው ብሏል

https://p.dw.com/p/3ydjp
Äthiopien I Parteiversammlung in Addis Ababa
ምስል Solomon Muche/DW

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጥሪ


ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ፣ከኢትዮጵያ በተፃራሪ መሰለፉን እንዲያቆም መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና ተቋማት ተወካዮች ጥሪ ቀረበ።የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዛሬ የአገራት አምባሳደሮችንና ተወካዮችን ጠርቶ ይህንን አዲስ አበባ ውስጥ ግልጽ አድርጓል።ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ እንዳትረጋጋ እና እንድትወድቅ የፀና ፍላጎት ያላቸው አገራትና ቡድኖች አሉ ይህም አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ታይቷል ብሏል። ዓለም አቁፉ ማኅበረሰብ በሽዎች የሚቆጠሩ ንፁኃን ዜጎች ለጥቃትና ጉዳት ከመዳረጋቸው በፊት ፈጥኖ ሊደርስ ይገባል ያለው የጋራ ምክር ቤቱ ፣የሚደረገው ያልተገባ ጣልቃ ገብነት ሊቆም እንደሚገባም አስገንዝቧል።የኢትዮጵያን ችግር ለጉዳት ከሚዳረጉ ሰዎች አንፃር መመልከት ሲገባ ከራስ ብሔራዊ ጥቅም ብቻ መቃኘት ኢሰብዓዊነት መሆኑንም የጋራ ምክር ቤቱ ለአምባሳደሮችና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ አብራርቷል።ጦርነት የችግር መፍትሔ አይሆንም ያለው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሁሉም ወገኖች ወደ ሰላም እንዲመጡ ዓለም በኢትዮጵያ ላይ የያዘውን አተያይም እንዲያስተካክል ጥሪውን አቅርቧል። 
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ 
 

Äthiopien I Parteiversammlung in Addis Ababa
ምስል Solomon Muche/DW