አይ ኤም ኤፍ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ28 የዓለም ደሃ ሀገራት አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ አጸደቀ
ማክሰኞ፣ መስከረም 26 2013ወረርሽኝ ያስከተለባቸውን ተጽዕኖ መቋቋም እንዲችሉ ታስቦ መሆኑን ድርጅቱ ይፋ አድርጓል። ድርጅቱ ባለፈው የሚያዝያ ወር ለ25 ሐገራት ተመሳሳይ የገንዘብ ድጋፍ አድርጎ ነበር።ድርጅቱ አሁን ያደረገው የገንዘብ ድጋፍ ሀገራቱ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ለአለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት IMF ለሚከፍሉት ዕዳ ፋታ የሚሰጥ እና ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስችል አስቸኳይ የጤና አገልግሎት እንዲያውሉት የሚሰጣቸውን ገንዘብ ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተመልክቷል። የገንዘብ ድጋፉ ከሚደረግላቸው ውስጥ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሃያ ሁለቱ አፍሪካውያን ሀገራት ናቸው። አፍጋኒስታን ፣ የመን ፣ ሃይቲ ፣የሶሎሞን ደሴቶች እና ታጃኪስታን ድጋፉ ከሚደረግላቸው ሃገራት ውስጥ ናቸው። የዕዳ እፎይታ ጊዜም ሆነ የገንዘብ ድጋፉን የሚያገኙት ሀገራት በተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ አደጋዎች ውስጥ ያሉ፣ በኮሮና ወረርሽኝ ብርቱ ጉዳት የደረሰባቸው እና ፍጹም ተጋላጭ ደሃ የሆኑ ሃገራት ናቸው። ማሊ የገንዘብ ድጋፉን ማግኘት የሚገባት ሀገር እንደሆነች የገለጸው ድርጅቱ አሁን ሀገሪቱን በማስተዳደር ላይ ያለው ወታደራዊ መንግስት በአለምአቀፉ ማሕበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት አለማግኘቱ እስኪረጋገጥ ድረስ ድጋፉን የማይለቅ መሆኑን አረጋግጧል።ድርጅቱ በቀጣዮቹ ሁለት አመታት ውስጥ 1.4 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ለሀገራቱ ለመስጠት እንደሚሰራም አስታውቋል።
ታምራት ዲንሳ
ነጋሽ መሐመድ