1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውድድር መር የቴሌኮም አገልግሎት በኢትዮጵያ 

ሰኞ፣ ጥቅምት 16 2013

በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ውስጥ እንደ ኢትዮ ቴሌኮም ራሳቸውን ችለው በሊበራላይዜሽን ወደ ገበያው የሚቀላቀሉና የራሳቸውን መሰረተ ልማት ዘርግተው የሚሠሩ ሁለት የውጭ የቴሌኮም ኩባንያዎች እስከ መጋቢት አልያም ሚያዝያ 2013 ዓ.ም ድረስ ሥራ ይጀምራሉ ተባለ።

https://p.dw.com/p/3kSa5
Äthiopien Debre Zeit  (Bishoftu) - Smartphone Nutzung
ምስል DW/T. Waldyes

አንድ ኩባንያም በፕራይቬታይዜሽን ገበያውን ይቀላቀላል ተብሏል


በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ውስጥ እንደ ኢትዮ ቴሌኮም ራሳቸውን ችለው በሊበራላይዜሽን ወደ ገበያው የሚቀላቀሉና የራሳቸውን መሰረተ ልማት ዘርግተው የሚሠሩ ሁለት የውጭ የቴሌኮም ኩባንያዎች እስከ መጋቢት አልያም ሚያዝያ 2013 ዓ.ም ድረስ ሥራ ይጀምራሉ ተባለ። በሌላ በኩል የኢትዮ ቴሌኮምን ዝቅተኛ የሀብት ድርሻ የሚገዛ እና አብሮ የሚሠራ አንድ ኩባንያም በፕራይቬታይዜሽን ገበያውን ይቀላቀላል ተብሏል። እነዚህ ኩባንያዎች ከፍተኛ የአገልግሎት ጥራት፣ ተወዳዳሪነት፣ ፍጥነትና የዋጋ ፍትሃዊነትን የሚያመጡ ናቸው ተብሎ ታምኖበታል። የኢትዮጵያ የኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳለው፦ ተቋማቱ ወደ ሥራ ሲገቡ ከደኅንነትና ሌሎች ጉዳዮች አንፃር በመንግሥት ከፍተኛ ክትትል ይደረግባቸዋል።

ሰለሞን ሙጬ 


አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ