1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውይይት፦ የተካረረው የህወሓት እና ኢህአዴግ ቅራኔ

እሑድ፣ ጥቅምት 16 2012

የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ኢህአዴግን ተችቷል። ይህንን ተከትሎ የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት በህወሓት መግለጫ የተነሱ ነጥቦችን የሚያጣጥል ምላሽ ሰጥቷል። የግንባሩ ሊቀመንበር አብይ አህመድም በስም ባይጠቅሱም ህወሓት ላይ ያነጣጠረ ትችት ሲሰነዝሩ ተደምጠዋል። የመቃቃሮቹ መንስኤዎች ምንድናቸው?

https://p.dw.com/p/3S1Pm
Äthiopien 40. Jahrestag TPLF
ምስል DW/T. Weldeyes

ውይይት፦ የተካረረው የህወሓት እና ኢህአዴግ ቅራኔ

የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ ለሰባት ተከታታይ ቀናት ካደረገው ስብሰባ በኋላ ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ እንደተቀመጠው የኢህአዴግ የውህደት ጉዳይ በግንባሩ እና በፓርቲው መካከል መሰረታዊ ልዩነት ፈጥሯል። ህወሓት “በመሰረተ ሀሳብ ደረጃ” እንደሚቀበለው የሚናገርለት ውህደት “በችኮላ እየተደረገ ነው” ሲል ይተቻል። የህወሓት አመራሮችም ከመግለጫው በፊትም ሆነ በኋላ በሚሰጧቸው ቃለመጠይቆች “ውህደቱ ጊዜውን ያልጠበቀ” እና “ከኢህአዴግ እምነት እና መተዳደሪያ ደንብ ውጪ” እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲጠቅሱ ይሰማል።

ህወሓት አራቱን የግንባሩ አባል ድርጅቶችን የሚያስተሳስር አንድ አመለካከት እና እምነት በሌለበት ሁኔታ ውህደት አይታሰብም የሚል አቋሙን ሲያንጸባርቅ ቆይቷል። የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ባለፈው ረቡዕ፣ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም.፤ በሰጡት መግለጫ ደግሞ ወደ ውህደት ለመምጣት ዋነኛው ልዩነት የተፈጠረው “አብዮታዊ ዲሞክራሲ” የተባለውን የኢህአዴግ ፕሮግራም ይዞ መቀጠል ላይ እንደሆነ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። 

በህወሓት እና በኢህአዴግ መካከል ያለው መቃቃር ገፊ ምክንያቶች የውህደት እና ድርጅቱ በሚከተለው ፕሮግራም ላይ የተፈጠሩ ልዩነቶች ብቻ እንዳልሆነ የሚያስረዱ የፖለቲካ ተንታኞች አሉ። ከዚያም የተሻገሩቱ ቅራኔዎች በህወሓት እና ኢህአዴግ መካከል ያለው ልዩነት ከጊዜ ወደጊዜ እየሰፋ እንዲመጣ እንዳደረገው ይገልጻሉ። በኢህአዴግ ላይ ተደጋጋሚ ወቀሳ እያቀረበ የሚገኘው ህወሓት በዚህ አካሄዱ “ከግንባሩ መለየቱ አይቀሬ ነው” ሲሉም ይተነብያሉ።  

የእዚህ ሳምንት የውይይት መሰናዷችን ትኩረትም ሰሞነኛው የኢህአዴግ እና የህወሓት ቅራኔ መካረር ነው። የህወሓት አመራር እና የመቀለ ዩኒቨርስቲ መምህር ዶ/ር ሺሻይ አማረ፣ የፖለቲካ እና የፖሊሲ ጉዳዮች ተንታኝ ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ እና የኢህአዴግን ጉዳዮች በቅርበት የሚከታተሉ የፖለቲካ ታዛቢ አቶ ዮናታን ተስፋዬ የውይይቱ ተሳታፊዎች ናቸው። 

ሙሉ ውይይቱን የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ማድመጥ ይችላሉ። 

ተስፋለም ወልደየስ 

እሸቴ በቀለ