1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውይይት ፤ ኦባሳንጆ ለኢትዮጵያ ሰላም ያስገኙ ይሆን?

ሰኞ፣ ኅዳር 6 2014

ኢትዮጵያ ዉስጥ አንድ ዓመት ያስቆጠረዉ ጦርነት፤ ብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድሎአል፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብን ደግሞ አፈናቅሎአል። ጦርነቱ ወደ ሰሜን ሸዋ አዉዱን እያሰፋ ነዉ ተብሎአል። በአፍሪቃ ኅብረት የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልክተኛ ኦሊሴንጎን ኦባሳንጆ፤ ለፀጥታዉ ምክር ቤት  እንደገለፁት ድርድር ለማካሄድ ሥራ ጀምረዋል።

https://p.dw.com/p/42wc7
Olusegun Obasanjo
ምስል Braima Darame

የኢትዮጵያ ጦርነት እና ዲፕሎማሲያዊዉ ጥረት

ኢትዮጵያ ዉስጥ አንድ ዓመት ያስቆጠረዉ ጦርነት፤ ብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድሎአል፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብን ደግሞ አፈናቅሎአል። ጦርነቱ ወደ ሰሜን ሸዋ አዉዱን እያሰፋ መሆኑም እየተዘገበ ነዉ። የተለያዩ መንግሥታት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፤ ተፋላሚ ኃይላት ተኩስ አቁመዉ፤ ልዩነታቸዉን በድርድር እንዲፈቱ፤ ዉግያዉ ትግራይ ዉስጥ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ቢያቀርቡም፤ እስካሁን ድረስ የሰላም መፍትሄ አልተገኘም። ተፋላሚ ኃይላት በየበኩላቸዉ እየዛቱ ደጋፊዎቻቸዉን ለተጨማሪ ዉግያ እያዘጋጁ ነዉ። በሳምንቱ መጀመርያ የተመድ የፀጥታዉ ም/ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለ 12ኛ ጊዜ ተወያይቶአል። በዉይይቱ ላይ አስተያየት የሰጡ ዲፕሎማቶች በሙሉ ሁሉም ተፋላሚ ሀይላት  ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ አቁመው ወደ ውይይት እንዲመጡ እና ሰላማዊመፍትሄ እንዲገኝ አሳስበዋል። ከኢትዮጵያ መንግሥት እና ከህወሓት መሪዎች ጋር በተናጠል ዉይይት ያደረጉት በአፍሪቃ ኅብረት የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልክተኛ የቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴንጎን ኦባሳንጆ፤ ለፀጥታዉ ምክር ቤት  እንደገለፁት ‹‹ሁለቱም ወገኖች ወደ ግጭት ያስገባቸው የፖለቲካ ልዩነት እንደሆነና ልዩነታቸውም በፖለቲካዊ ውይይት መፍትሔ ማግኘት ይችላል ብለው እንደሚያምኑ በተናጠል ገልጸውልኛል፤›› ብለዋል። ነገር ግን የተከፈተው ዕድል ትንሽና ያለው ጊዜም በጣም አጭር እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል፤” ሲሉ አጽኖት ሰተዋል። ኦባሳንጆ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥትና ሕወሓት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ልዩነታቸውን በውይይት እንዲፈቱ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሊሰጥና ሊያበረታታ ይገባል፤ ሁሉም የግጭቱ ተሳታፊ ወገኖች ያለቅድመ ሁኔታና ጊዜ ሳይሰጡ አጠቃላይ የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ የፀጥታ ምክር ቤቱ ጥሪ ማቅረብ ይኖርበታል፤›› ሲሉም ነዉ ያሳሰቡት።

በኢትዮጵያ ለዓመት የዘለቀዉ ደም አፋሳሽ ግጭት እንዲቆም እና የሰላም ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን በተፋላሚ ሀይላቱ በኢትዮጵያ ህዝብ እና በዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ምን መደረግ አለበት ?ስምምነቱስ  ስኬታማ ይሆናል ወይ? በዚህ ዉይይት ላይ ሃሳባቸዉን የሚያካፍሉን ወ/ሮ ሰላማዊት ካሣ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ፤ እንዲሁም አቶ ሙላቱ ገመቼ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)  ምክትል ሊቀመንበር ናቸዉ። ዮናስ መብራቱ በድሪደዋ ዩንቨርስቲ አስተማሪ የነበሩ በአሁኑ ወቅት በጀርመን ኑረምበርግ ኤርላንገን ለዶክትሪት ማዕረግ ትምህርት በመከታተል ላይ የሚገኙ፤ ናቸዉ። ዶ/ር ዮናስ አዳዬ በአዲስ አበባ ዬንቨርስቲ የሰላምና ደህንነት ተቋም ኃላፊ በዉይይቱ ለመሳተፍ ቃል ገብተዉ ነበር ስልኩን አላነሱልንም።

 

አዜብ ታደሰ