ውይይት «በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን መድረክ ድልድይ»
ማክሰኞ፣ ግንቦት 3 2013ማስታወቂያ
መቀመጫውን አውራጳ ውስጥ ያደረገው «በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን መድረክ ድልድይ» የተባለው ስብስብ በኢትዮጵያ በቅርቡ ሊካኼድ ቀጠሮ ስለተያዘለት ሀገር አቀፍ ምርጫ ውይይት አድርጓል። የበይነ-መረብ ጉባኤው ባለፈው ሣምንት ቅዳሜ ሲካኼድ ለለሦስተኛ ጊዜ ነበር። የበይነ መረቡ የውይይት ርእስ፦ «የዘንድሮው የኢትዮጵያ ምርጫ ተግዳሮቶች እና የመፍትኄ አቅጣጫ» የሚል ነበር። የውይይቱ ተሳታፊዎች ሦስት ምሁራን ስለምርጫው ያላቸውን ምልከታ አሰምተዋል። ውይይቱን የብራስልሱ ወኪላችን ተከታትሎ ልኮልናል።
ገበያው ንጉሤ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ