ውይይት፦ የኢትዮጵያ ምርጫ ዝግጅት
ሰኞ፣ የካቲት 11 2011ማስታወቂያ
እስካሁን በተያዘዉ ዕቅድ መሠረት ኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ የምታስተናግድበት ጊዜ ከዓመት በላይ ብዙም አልቀረዉም።የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮችና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባለሥልጣናት ግን የቦርዱን ኃላፊነት፣ አሠራር፣ አወቃቀር፣ደንብንና ምናልባትም መሪዎቹን ለማሻሻልና ለመቀየር ገና እየተወያዩ ነዉ።የብዙ አካባቢ ፀጥታም አስተማማኝ አይደለም።በዚያ ላይ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ የስታትስቲክስ መስሪያ ቤት የሐገሪቱን ሕዝብ ለመቁጠር ገና እየተዘጋጀ ነዉ።በዚሕም ምክንያት የመራጩን ሕዝብ ትክክለኛ ቁጥር በዉል መናገር አይቻልም።እስካሁን ባለን መረጃ ግን ከ36 እስከ 40 ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ድምፅ ይሰጣል ተብሎ ይገመታል።ተፎካካሪዎች፣ አስመራጭና ተመራጮች በዚሕ አጭር ጊዜ ዉስጥ ተወያይተዉ፣ ተስማምተዉ፣ አወዳድረዉ፤ ወይም ተወዳድረዉ፣ ሐገር አረጋግተዉ፣ ሕዝብ ቆጥረዉ ነፃና ትክክለኛ ምርጫ ማድረግና መምራት መቻላቸዉ እያጠያየቀ ነዉ።አጠያያቂዉ ጉዳይ የዉይይታችን ትኩረት ነዉ።ሰወስት እንግዶች አሉን።
ነጋሽ መሐመድ