ሕዝቡየምርጫ ዉጤት በመጠባበቅ ላይ ነዉ፤
ሐሙስ፣ ነሐሴ 4 2009ማስታወቂያ
ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች የምርጫዉን አያያዝ ማድነቃቸዉ ቢነገርም በናይሮቢና ሌሎች አጎራባች አካባቢዎች ሕዝቡ ከወዲሁ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ መጀመሩን ዘገባዎች ያመለክታሉ። ፖሊስም በአስለቃሽ ጋዝ ጎዳና የወጡት ለመበተን መሞከሩም ተገልጿል። የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን የምርጫዉን የኢንተርኔት መረጃ ለመስበር ተሞክሮ መክሸፉን አስታዉቋል። ከዓመታት በፊት በምርጫ ዉዝግብ ምክንያት የደረሰዉ የሰዉ ሕይወት ጥፋት እና የንብረት ዉድመት ጠባሳ ያልሻረባት ኬንያ አሁንም ወደዚያዉ እንዳታመራ ጥንቃቄ እየተደረገ ነዉ። ከናይሮቢ የፖለቲካ ተንታኝ አቶ ፍቅረማርያም መኮንን ስለዛሬዉ ድባብ ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በስልክ አነጋግሬያቸዋለሁ።
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ