1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዉይይት፤ የትግራዩ ጦርነት፤ የዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ዉትወታና የኢትዮጵያ አቋም

እሑድ፣ ታኅሣሥ 4 2013

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጣልቃ እንዳይገባ መግለጫ ከማውጣት አልፎ፤ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፤ ወደ ተለያዩ ሃገራት በመጓዝ ጉዳዩን እንዲያስረዱ አድርጓል። ነገሩ ሕግን በማስከበር ሂደት ብቻ የሚፈታ መሆኑን በመግለጽም የሀገር ክህደት ፈጽሟል ካለው ቡድን ጋር መደራደር የሚለውን ሃሳብ አልተቀበለም።

https://p.dw.com/p/3mdGd
USA Zeitungen
ምስል Getty Images/S. Olson

ዉይይት፤ ትግራይ በአፋጣኝ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መጀመር አለበት

የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና «ሕወሓት» ትግራይ ክልል ዉስጥ የሚያገርጉትን ውጊያ የተለያዩ የሰብዓዊ እና ርዳታ ድርጅቶች እየገለፁ ነዉ። በመንግሥት እና መንግሥት ለሕግ አቀርበዋለሁ የሚላቸዉ  የሕወሓት መሪዎች ውጊያውን አቁመዉ እንዲደራደሩና መፍትሄ እንዲያገኙ የአፍሪቃ ሕብረትን ጨምሮ የተመድ እንዲሁም የአውሮጳ ሕብረት ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት የውጊያውን መንስኤ በመግለፅ «ጉዳዩ የውስጥ ችግር ነውና»  ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጣልቃ እንዳይገባ መግለጫ ከማውጣት አልፎ፤ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፤ ወደ ተለያዩ ሃገራት በመጓዝ ጉዳዩን እንዲያስረዱ አድርጓል። ነገሩ ሕግን በማስከበር ሂደት ብቻ የሚፈታ መሆኑን በመግለጽም የሀገር ክህደት ፈጽሟል ካለው ቡድን ጋር መደራደር የሚለውን ሃሳብ አልተቀበለም። ከሳምንት በፊት በትግራይ የሚያካሂደውን ውጊያ ማጠናቀቁን ያመለከተው የኢትዮጵያ መንግሥት፤ በቀጣይ በጦርነቱ የተጎዱ የትግራይ መሠረተ ልማቶችን መጠገን የተፈናቀሉ እና የተሰደዱ ነዋሪዎችን ወደ መኖሪያቸው የመመለስ ሥራ ጀመሩንም አሳውቋል። መንግሥት አብቅቷል ያለውን ውጊያ አሁንም ለመቀጠሉ ዘገባዎች ደርሰዉኛል የሚለው ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ በጦርነቱ ለተጎዱትና ርዳታ ለሚያስፈልጋቸው አስፈላጊውን ሰብዓዊ ርዳታ ለማድረስ ወደ አካባቢው መግባት እንዲቻል ጠይቋል። የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ኮሚሽነር በበኩሉ በዉግያዉ የደረሰዉ ጉዳት በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ጠይቆአል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ እስካሁን ከአቅም በላይ የሆነ ነገር ባለመከሰቱ ገለልተኛ ምርመራ የሚለውን እንደማይቀበል ነዉ ያሳወቀዉ። የዕለቱ ውይይታችን  የኢትዮጵያ መንግሥት አቋም ፤ የውጭ መንግሥታት እና የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ አቋሞች  ይመለከታል።  በዚህ ዉይይቱ የተሳተፉት ፤

በጀርመን ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ፣ በቼክ ሪፐብሊክ፣ በፖላንድ ፣ በስሎቫክ እና በዩክሬን የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርና ልዩ መልዕክተኛ ሙሉ ሰሎሞን ብዙነህ፤ ልዑል ዶክተር አስፋወሰን አሥራተ ካሳ፤ በጀርመን የአፍሪቃና የመካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮች አማካሪ እና የታወቁ ደራሲ፤ እንዲሁም ጠበቃ ዮሃንስ መብራቱ በድሪደዋ ዩንቨርስቲ አስተማሪ የነበሩ በአሁኑ ወቅት በጀርመን ኑረምበርግ ኤርላንገን ለዶክትሪት ማዕረግ ትምህርት በመከታተል ላይ የሚገኙ  ናቸዉ።

ሙሉ ዉይይቱን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን!

አዜብ ታደሰ