1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወጣት አካል ጉዳተኞች የተሳተፉበት የፋሽን ትርዒት

ዓርብ፣ ጥቅምት 16 2011

አካል ጉዳተኞች በህብረተሰቡ ዘንድ በኢኮኖሚው፣ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በሌሎችም አስተዋጽኦ እያበረከቱ ቢገኙም ካለባቸው አካላዊ እክል የተነሳ ያሉባቸው ችግሮች አሁንም አልተቀረፉም፡፡ ለዚህም በዋነኛነት እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው በህብረተሰቡ ዘንድ ስለአካል ጉዳተኞች ያለው የተሳሳተ አመለካከት ነው።

https://p.dw.com/p/37GGj
Äthiopien Addis Abeba Modenschau für Behinderte
ምስል Rigbe Hagos

በተጨማሪም ፣ በብዙ የስራ መስኮች ምቹ ሁኔታ ስላልተፈጠረላቸው አካል ጉዳተኛነት የመገለል እጣ ያጋጥማቸዋል። ይህ ችግር ከሚታይባቸው መስኮች አንዱ የፋሽን ሙያው ነው።  ችግሮቹን ለማስወገድ እና የአመለካከት ለውጥ ለማስገኘት በፋሽኑ ዘርፍ ካለፈው ዓመት ወዲህ ውጥን  ተጀምሯል።

ነጃት ኢብራሂም

አርያም ተክሌ