ወጣቱ በግብርና የማይሰማራበት ችግር ላይ ውይይት ተካሄደ
ሐሙስ፣ ኅዳር 11 2012ማስታወቂያ
በአፍሪካ በተለይ በኢትዮጵያ የነገው የግብርና ዘርፍ በወጣቶች የሰው ኃይል ላይ መመስረት እንዳለበት በመታመኑ ቡድን ሰባት ተብሎ የሚጠራው በኢንዱስትሪ የበለጸጉ ሀገራት ስብስብ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶታል። የቡድን ሰባት ተወካዮች ከአፍሪካ ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት የተውጣጡ እና አርአያ ይሆናሉ ከተባሉ ወጣቶች ጋር ጉድለቶች ናቸው የሚባሉትን ለይቶ ለማውጣት በአዲስ አበባ ውይይት አካሄደዋል። በኢትዮጵያ እና በምስራቅ አፍሪካ የዘንድሮው የቡድን ሰባት ሊቀመንበር ፈረንሳይ እንደመሆኗ በአውሮፓ ህብረት የዘርፉ ተጠሪ ኦርያን ባርቴሌሜ ስብሰባው መካሄድ ያስፈለገበትን ምክንያት ለዶይቼ ቬለ አብራርተዋል።
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ተስፋለም ወልደየስ
ማንተጋፍቶት ስለሺ