1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወደ መቀሌ የመንገደኞች በረራ ነገ ረቡዕ ታኅሣሥ 19 ይጀምራል

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 18 2015

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ረቡዕ ታኅሣሥ 19 ጀምሮ ወደ መቀሌ የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት እንደሚጀምር አስታወቀ። የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ ተቋርጦ የቆየው የአውሮፕላን አገልግሎት የሚጀምረው የመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ ለበረራ አገልግሎት ዝግጁ መሆኑ ከታየ በኃላ መሆኑ ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/4LSc3
Äthiopien Addis Abeba Airport Ethiopian Airlines
ምስል Mas Agung Wilis/Zuma/IMAGO

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ረቡዕ ታኅሣሥ 19 ጀምሮ ወደ መቀሌ የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት እንደሚጀምር አስታወቀ። የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ ተቋርጦ የቆየው የአውሮፕላን አገልግሎት የሚጀምረው የመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ ለበረራ አገልግሎት ዝግጁ መሆኑ ከታየ በኃላ መሆኑ ተገልጿል።

Äthiopien Addis Abeba
አዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፍያምስል Solomon Muchie/DW

ጆቼ ቬለ ( DW ) በአዲስ አበባ ሒልተን እና ጣይቱ ሆቴሎች ውስጥ በሚገኙ የአየር መንገዱ እና የኮሚሽን የአየር በረራ ቴኬት መሸጫ ማዕከላትን ተመልክቶ እንዳረጋገጠው የመቀሌ መንገደኞች ከጥዋቱ ጀምሮ ቲኬት ሲቆርጡ ውለዋል። እስከ ቀጣዩ ሳምንት ሰኞ ድረስ ባሉት ቀናት ውስጥ ቲኬት ተሸጦ ማለቁንም ለማወቅ ችለናል።

አየር መንገዱ ለጊዜው በቀን አንድ በረራ መፍቀዱንም ከቲኬት መሸጫ ማእከላት ያገኘነው መረጃ ያሳያል። 

ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ የመንገደኞች ምልልስ ያደርግባቸው ከነበሩ መስመሮች አንዱ ከአዲስ አበባ መቀሌ - ከመቀሌ አዲስ አበባ ያለው መስመር ነበር።ላለፉት ሁለት ዓመት እና በላይ ግን ይህ አገልግሎት ተቃርጦ ቆይቷል። አየር መንገዱ ከነገ ጀምሮ ወደ መቀሌ በረራ መጀመሩን እንዳስታወቀ ትኬቶች በፍጥነት በአካልም በኢንተርኔት መላም ተቆርጠዋል።

በአካል ሦስት ሰዎች ሄደው ቲኬት እንደቆረጡ የተናገረችው የኮሚሽን ቲኬት መቁረጃ ቢሮ ሰራተኛ ቲኬቶች በፍጥነት መቆረጣቸውን ለዶቼ ቬለ ተናግራለች።

Äthiopien Addis Abeba Nationaltheater
አዲስ አበባ ከተማ ምስል Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ መቀሌ እንዲሁም ከመቀሌ አዲስ አበባ ለአንድ ሰው ምን ያህል እያስከፈለ እንደሆን ለማወቅ ያደረኩት ጥረት ባይሳካም በወኪልነት የሚሰራው የቲኬት ቢሮ ሰራተኛ ግን የግል ድርጅት እንደመሆኑ የሚሰሩበትን ዋጋ ገልጻልናለች። "ከመቀሌ አዲስ አበባ አምስት ሺህ ብር ነው" ብላለች።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ለሀገር ውስጥ መገናኛ አውታሮች በሰጡት መግልጫ ትናንት ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን እና ከአየር መንገዱ የተውጣጣ ወደ መቀሌ የተላከ የባለሙያዎች ቡድን የመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ ለበረራ አገልግሎት ዝግጁ መሆኑን ተመልክቶ መመለሱን ገልፀዋል። በዚህም መሰረት የአውሮፕላን ማረፊያው ለበረራ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት መጀመሩ ተለያይተው የቆዩ ቤተሰቦችን ከማገናኘት ባለፈ የእርዳታ እቅርቦት ሥራዎችን እንደሚያቀላጥፍ እንደሚያግዝም ዋና ሥራ አሥፈፃሚው ገልፀዋል።

አየር መንገዱ በቅርብ ጊዜ በሌሎች ትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ የአውሮፕላን ማረፊያዎችም ሥራውን ይጀምራል ተብሏል።

 

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ