1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወቅታዊው የፖለቲካ ቀውስ እና የኢትዮጵያ አንድነት ጥያቄ

እሑድ፣ ሐምሌ 7 2011

ላለፈው አንድ ዓመት የለውጥ ሂደት የምታስተናግደው ኢትዮጵያ ከጥቂት ወራት ወዲህ ውጥረት እና ፍጥጫ መገለጫዋ ሆነዋል። ከዓመት በፊት የከፋ አደጋ ላይ ደርሳለች ስትባል ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በራሱ ውስጥ ባካሄደው መሸጋሸግ ያመጣው ለውጥ  ድባቡን ለውጦ ተስፋ ዘርቶባት ሕዝቡም አረፍ ብሎ ነበር።

https://p.dw.com/p/3LztD
EPRDF Logo

«ትኩረት የሚያሻው የሀገር አንድነት ጉዳይ»

እያደር ብልጭ ያሉት አንዳንድ አጋጣሚዎች እና ከመንግሥት ወገን ጥርት ያለ መረጃ እጥረቱ እንዳለ ሆኖ ከድንገቴው የከፍተኛ ወታደራዊ እና ፖለቲካ ባለሥልጣናት ግድያ በኋላ የጋዜጠኞች እና የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እስራት ዳግም ሌላ የስጋት ምክንያት ሆኗል። በሌላ በኩል በክልሎች መካከል የሚታየው ፉክክር እንዲሁም በገዢው ግንባት አባላት መካከል ጎልቶ የወጣው አለመግባባት ኢትዮጵያን አቅጣጫው ወዳልታወቀ ዕጣ ፈንታ እየገፋት እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ። የክልል እንሁን ጥያቄዎች፣ የድንበር እና ግዛት ጉዳዮች ሀገር እንደ ሀገር የመቀጠሏን ጉዳይ አሳሳቢ እና እንቆቅልሽ አድርጎታል። ወቅታዊው የፖለቲካ ቀውስ እና የኢትዮጵያ አንድነት ጥያቄ የዚህ ሳምንት የዶይቼ ቬለ እንወያይ ርዕስ ነው። ሙሉ ውይይቱን ከድምፅ ዘገባው ይከታተሉ። 

ሸዋዬ ለገሠ