1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኮሮና፤የአፍሪቃዉያን ድርብ ስጋት

ቅዳሜ፣ መጋቢት 26 2012

የኮረናወረርሽኝንን ለመከላከል የተደረገዉ የእንቀስቃሴ ገደብ በአፍሪቃ የፈጠረዉ የኢኮኖሚ ጫና እንዲሁም በጀርመን በአነስተኛ የንግድ ስራ የተሰማሩ አፍሪቃዉያን  በዚህ ወቅትእያጋጠማቸዉ ያለዉን ቸግር ይዳሰሳል። 

https://p.dw.com/p/3aSZR
Coronavirus Südafrika Township Khayelitsha bei Kapstadt Ausgangssperre
ምስል AFP/R. Bosch

ኮሮና፤የአፍሪቃዉያን ድርብ ስጋት

ዓለምንስጋት ላይ የጣለዉ የኮቪድ-19 በሽታ በአፍሪካም እስካሁን በሺዎች የሚቆጠሩ  ሰዎች በዚህ  ወረርሽኝ መጠቃታቸውንናበመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ መሞታቸዉን መረጃዎች ያሳያሉ።በመሆኑም ሀገራት ይህንን ወረርሽኝ ለመቆጣጠር የተለያዩ ርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ።እነዚህ ርምጃዎች  የሰዎችን የለትተለትእንቀሰቃሴና መደበኛ  ሰራ የሚገድቡበመሆናቸው  አብዛኛዉ ህዘብበድህነት ለሚኖርባት አፍሪቃ ርምጃዎቹ ፈታኝ ሆነዋል።

ይህወረርሽኝ በአህጉሪቱ በ49 ሀገራት የተከሰተ ሲሆን ሩዋንዳና ቱኒዚያና   ቀደም ብሎከተከሰተባቸው ሀገራት መካከል በመሆናቸው ሰርጭቱን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ክልከላም ቀደም ብለው የጀመሩ ሀገራት ናቸው።ቆይታም ደቡብ አፍሪቃ  በጎርጎሪያኑ መጋቢት 26 ቀን ወደ ሰባት መቶ የሚጠጉ ዜጎቿ በቫይረሱ መጠቃታቸው ከተረጋገጠ ከሁለት ቀን በኋላ ወረርሽኙን ለመቆጠር የሚደረገዉን እንቅስቃሴ የመግታት ርምጃ ጀምራለች። ያምሆኖ  ርምጃዉ ለሀገሪቱዜጎች ቀላል አይደለም። ብዙ ደቡበ አፍሪቃዉያን፤ በተለይም በከተሞች ፤በድህነት የሚኖሩና ንጹህ የመጠጥ ዉሃ በአግባቡ የማያገኙ ናቸዉ።አኗኗራቸውም ቢሆን መደበኛ ባለሆነ አሰፋፈር በአንድ  አካባቢ በርካታሰዎች ተሰባስበዉ የሚኖሩ በመሆናቸው በሽታውን ለመከላከል የሚረዱት ማኅበራዊ ፈቀቀታና እጅን በአግባቡ መታጠብ  የመሳሰሉትን ተግባራትበአግባቡ ለማከናወን የሚያስችል ሁኔታ የለም።ገቢያቸዉም  ቢሆን ከዕለትጉርስ የሚያልፍ አይደለም።  በሀገሪቱ በተለይ ከጆሃንስበርግ ከተማ ወጣ በሎ በሚገኘው ዲፕሰሎትና ከኬፕታወን ከተማ ወጣ በሎ በሚገኘው ዴልፍት የተባሉ ቦታዎች ከፍተኛ ድሀነት፣ሰራ አጥነት፣እንዲሁም ኤች.አይቪ ኤድስ፣የሳንባ ነቀርሳና የሰኳር በሽታ በከፍተኛ መጠን የተስፋፋባቸው ቦታዎች ናቸው።

እነዚህበድህነት ኑሮአቸዉን የሚገፉ ሰዎች  በኮረና ወረርሽኝሳቢያ ሁሉም ነገር ከተዘጋ ወዲህ ደግሞ ኑሮአቸው የበለጠ አስቸጋሪ ሆኗል። የችግሩ ስፋት ይለያይ እንጅ ሌሎቹ የአፍሪቃ ሀገራትም ቢሆን የኮሮና ወረርሽኝ የሚያሳደረው ተፅዕኖ ቀላል አይደለም። ምክንያቱም ደካማ የጤና ስርዓት፣ ድህነትና ስራ አጥነት መጠኑ ይለያይ እንደሁ እንጅ የአፍሪቃ ሀገራት የሚጋሩት ችግር ነዉና። በናይጄሪያ  ሌጎስ በቀንስራ የሚተዳደሩት የማያ ዲቦላ ህይወት ይህንን ያረጋግጣል። «ይህ የዕንቅስቃሴ ገደብ አስጨንቆኛል። ለእኔ በጣም የሚያበሳጭ ነገር ነው።እንዴት ሰው ሃያ አራት ስዓት ቤት ይቀመጣል።በባንክ ደበተሬ ከአንድ ዶላር ብቻ ነው ያለኝ።ሶስት ለጆች አሉኝ።»  የሰዎችን እንቅስቃሴመገደብ  እና ሌሎችዕርምጃዎችን መዉሰድ የኮረናን ስርጭት ለመግታት ውጤታማ መሆኑ ከቻይና ተሞክሮ መረዳት ይቻላል ።ነገር ግን ይህ ርምጃ በአፍሪቃ በተለይም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ በሚገኙ ሰዎችና በአነስተኛ መካከለኛ የንግድ ተቋማት ላይ  የሚያሳድረው የአኢኮኖሚጫና  ቀላል አይደለም፡፡

ለአፍሪቃእርዳታ በመለግስ  የሚታወቁት ምዕራባዉያንምበራሳቸዉ ችግር የተጠመዱበት ወቅት መሆኑ ደግሞ ችግሩን የበለጠ ያደርገዋል። ለዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶችም ቢሆን ለአፍሪቃ ችግር ምላሽ  ለመስጠት ወቀቱአስቸጋሪ  መሆኑን ኤም.ኤስ.ኤፍ የተባለዉ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅት የአፍሪቃ ተጠሪ ይናገራሉ። « በመጀመሪያ ደረጃ ሁሉም ሀገሮች  ድንበሮቻቸዉን ዘግተዋል።አዉሮፓ፣አፍሪቃ፣አሜሪካ ሁሉም ዘግተዋል።ስለዚህዓለም አቀፍ የእርዳታ ደረጀቶች በአፍሪቃም ይሁን በማንኛዉም ቦታ ተንቀሳቀሶ ዕርዳታ ማቅረብ አይችልም። እዚያዉ አፍሪቃ ውስጥ ቢሆን አይቻልም። ምክንያቱም ድንበሮች ተዘግተዋል» እናምአፍሪቃ የተጋረጠባትን ችግር ለመወጣት የሚሻለው የሀገር ዉስጥ ሀብትን መጠቀም ነው ይላሉ።ያም ሆኖ ችግሩ  ሙሉ ለሙሉለአፍሪቃ መንግስታት የሚተው አይደለም፡፡ወረርሽኙ በአህጉሪቱ  የጤናና የኢኮኖሚሁኔታ ላይ የሚይሳድረውን ተፅኖ ለመቀነስ በአቅራቢያ የሚገኙ የበጎ አድራጊ ድርጅቶችና ግለሰቦች  እንዲሁም የሀይማኖትተቋማት ሊተባበሩ ይገባል። ተቋማቱ የሚያስተምሩትን በጎነት ለመተግበርም ይህ ወቅት እድል የሚስጥ ይሆናል።

በአነስተኛ የንግድ ስራ የተሰማሩ አፍሪቃዉያን በጀርመን

በርካታየዓአለም ሀገራትን ስጋት ላይ ጥሎ የሚገኘው የኮረና ወረረሸኝ የዳባረ ኢኮኖሚና ዘመናዊ ቴከኖሎጅ ላላት ሀገር ጀርመንም ፈታኝ ሆኗል።ወረርሽኙ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቀሰቃሴ የገታ ሲሆን ትምህርት ቤቶችና መስሪያ ቤቶች ተዘግተዋል፣ መደበኛ የሰዎች እንቀስቃሴ ተሰተጓጉሎ ሰዎች ቤታቸው መዋል ከጀመሩም ሳመንታት ተቆጥረዋል።የቫይረሱን ሰርጭት ለመግታት የተደረገዉ ይህ ርምጃ በሀገሪቱ በአነስተኛ የንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ አፍሪቃዉያን ሁኔታዉ አስቸጋሪ ሆኗል። በተለያዩ የጀርመን ከተሞች የሚገኙ የአሪቃዉያኑ ምግብ ቤቶች፣የፀጉር ሳሎኖችና ሱቆች በመዘጋታቸው ከባድ የኢኮኖሚ ጫና እያጋጠማቸው ነዉ።ከነዚህም መካከል  የ44 አመቱካሚሮናዊዉ ጃስፓ አንቻንግስ አንዱ ናቸው።

ጃሰፓየተጠበሰ  ደሮና ሌሎችምግቦችን በተንቀሳቃሽ የምግብ መያዣ መኪና በበርሊን ከተማ አዉራ ጎዳናዎች  ይሸጡ ነበር።የርሳቸዉንምግብ ለመግዛት አዉራ ጎዳናዉን በሰልፍ ይሞሉት የነበሩት ደንበኞቻቸውም በርከት ያሉ ነበሩ። ካለፉት ሳምንታት ወዲህ ግን ሁኔታው ተቀይሯል ይላሉ።  «አብዛኛዎቹ ደንበኞቻችንበአቅራቢያው ከሚገኙ መስሪያ ቤቶች የሚመጡ ናቸው።ስለዚህ ቢሮዎች ሰለተዘጉና ሰዎች ቤታቸው ሆነው እየሰሩ በመሆናቸው  በአሁኑ ወቅትብዙ ደንበኞች የሉንም ፡፡ ስለሆነም ሁኒታዉ ለእኛ ከባድ ነው ፣ ምክንያቱም በመንገድ ላይ ምንም ሰዉ የለም ፡፡በመንገድ የሚያልፉት በጣም ጥቂት ሰዎች ናቸው ፡፡ ይህ ወቅት ለእኛ በጣም ፈታኝና ከባድ ወቅት ነው ፡፡»

ከ 40 አመት በፊት ከወላጆቻቸዉ ጋር ከዲሞከራቲክ ኮነጎ ወደ በርሊን ከተማ የመጡት ካሎንጂ ታሻባ ሌላዉ የችግሩ ገፈት ቀማሽ ናቸው፡፡ የእሳቸው ድርጅት ለሙዚቀኞች የመለማመጃ ክፍሎችን ያከራያል ፣ለልጆች የሙዚቃ ትምህርቶችን ያዘጋጃል እንዲሁም ለባለሙያዎች የቀረፃ  ክፍሎችን ያከራያል።በአሁኑወቅት ግን እነዚህን እንቅስቃሴዎች አብዛኛዎቹን መሰረዝ ነበረባቸው። በዚህ የተነሳ ታሻባ  አሁን ትልቅችግር ገጥሟቸዋል። ምክንያቱም ስራ ቢቆምም ክፍያና ወጪ ይቀጥላልና። «ለልምምድ ክፍሎቻችን የቤት ኪራይ መክፈል አለብን። እና ደንበኞቹ እንዲመጡ ካልተፈቀደ በዚህ ጊዜ ውስጥ መንገድ መፈለግ አለብን»

እንደአብዛኛወቹ ነጋዴዎች ሁሉ ታሻባ ከመንግስት እርዳታ ለማግኘት አመልከተዋል። የጀርመን መንግሥት እና የበርሊን  ከተማ አስተዳደርለመካከለኛና አነስተኛ ኩባንያዎች እስከ 15 ሺህ  ዩሮ ድጎማይሰጣል፡፡ብዙ የኩባንያ ባለቤቶች  ይህ ገንዘብከደረሰባቸዉ ኪሳራ አንፃር በጣም አነስተኛ  ነው ይላሉ።ታሻባ ግን ድጎማዉ በቂ ነው ይላሉ። «ለእኛ እና ለአርቲስቶች የተሰጡ ዕድሎችን አደንቃለሁ ። አፍሪካ ውስጥ የሚኖሩ ብዙ አርቲስቶችንም አውቃለሁ።በአሁኑ ወቅት አንድ ሰው እዚህ በመኖሩ ብቻ ደስተኛ ሊሆን ይችላል።»

እንደጀርመን ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት  በሀገሪቱ ከሚገኙትኩባንያዎች በአሁኑ ወቅት 90 በመቶ የሚሆኑት ኪሳራ ደርሶባቸዋል። ከእያንዳንዱ አምስት ኩባንያ አንዱ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል። በርካታ የአፍሪካ ምግብ ቤቶች ፣ የፀጉር ቤቶቸና  ሱቆችም  ሁኔታው ከባድ ሆኗል። በዚህ የተነሳ  የአመልካቾች ቁጥርከፍተኛ በመሆኑ ሁሉንም ማዳረስ አልተቻለም።አንዳንድ አመለካቾችም  ለሁሉም በቂገንዘብ ስለመኖሩም ጥረጣሬ ገበቷቸዋል።ያም ሆኖ የመኪና ላይ የምግብ ንግዳቸው እንዲያንሰራራ ጃስፓ አንቻንግም የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያገኙ ተስፋ ያደርጋሉ ፡፡ «አሁን ባለው የስራ ጉዳይ ንግዱን መዘጋት ካለብኝና ከነ አካቴዉ ስራ ካቆመኩ፤ አሁን ባለው  ሁኔታ ሥራማግኘት ይከብዳል ፡፡ ያ እኔን የመንግስት  ላይ ጥገኛእንድሆን ያደርገኛል። ያንን ደግሞ ማድረግ አልፈልግም። ከመንግስት ድጋፍ ደስተኛ ሊሆን ይችላል።»ለማግኘት የማመልከት እድሉን ካገኘሁ በእርግጠኝነት የንግድ ስራዬ አይዘጋም።»ካሚሮናዊዉጃስፓ አንቻንግስ  ከሳምንታት በፊትጥሩ ገቢ ያስገኝላቸው የነበረው የጎዳና ላይ ንግዳቸው በመቀዘቀዙ ጭር ባለዉ የበርሊን ጎዳና የምግብ መሽጫ መኪናቸዉ ላይ  ሆነዉ ሲተከዙይውላሉ።እናም ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር  በዚህ አስቸጋሪ ወቅት  ጥሩ ነገርእንዲመጣ ተስፋ ማድረግ ብቻ ነው ፡፡

 

ፀሐይ ጫኔ

ነጋሽ መሐመድ