1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኮሮናን በተመለከተ የጀርመን ሚኒስትሮች ስብሰባ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 4 2013

ጀርመን የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭትን ለመግታት የምታደርገዉን ጥረት አጠናክራ ቀጥላለች። የጀርመን ፌድራል መንግሥት እና የክፍላተ ሃገራት ሚኒስትሮች ፖለቲከኞች፤ በሃገሪቱ የኮሮና ክትባትን ለሕዝቡ ለማዳረስ ዛሬ ከቀትር በኋላ ዉይይት ተቀምተዋል።

https://p.dw.com/p/3yo59
Berlin | Pressekonferenz: Angela Merkel
ምስል Clemens Bilan/Getty Images

ከሚቀጥለዉ ወር ጀምሮ የኮሮና ነጻ ምርመራ አይኖርም

ጀርመን የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭትን ለመግታት የምታደርገዉን ጥረት አጠናክራ ቀጥላለች። የጀርመን ፌድራል መንግሥት እና የክፍላተ ሃገራት ሚኒስትሮች ፖለቲከኞች፤ በሃገሪቱ የኮሮና ክትባትን ለሕዝቡ ለማዳረስ ዛሬ ከቀትር በኋላ ዉይይት ተቀምተዋል። በጀርመን እስከዛሬ ይሰጥ የነበረዉ የነጻ የኮሮና ምርመራ ከሚቀጥለዉ ወር ጀምሮ በክፍያ እንደሚሆንም ተመልክቶአል። በሌላ በኩል ክትባት ያልተከተበ ከኮሮና ነፃ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ እንዳለበትም ተነግሮአል። ክትባቱን ያገኙ ዜጎች በሙሉ ግን የኮሮና ተኅዋሲ መከላከያ ክትባትን መዉሰዳቸዉን የሚያሳይ ኤሌክትሮኒክስ መታወቅያ ይዘዋል። በጀርመን የኮሮና ክትባትን ያልወሰደ ሰዉ የወደፊት እጣዉ ምን ይሆን? የጀርመን መንግሥትን ዉሳኔ እና በጀርመን የኮሮና ስርጭት እና መከላከያዉ፤ ብሎም የነዋሪዉን አስተያየት በተመለከተ የበርሊኑን ወኪላችንን ጠይቀነዋል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ