1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቦሪስ ጆንሰን  የጤና ይዞታ 

ሰኞ፣ መጋቢት 28 2012

ኮሮና ብዙ ሰዎችን በገደላባቸው ስፓኝ ኢጣልያ እና ፈረንሳይ ባለፉት  ቀናት በበሽታው የሞቱና የሚያዙትቁጥር እየቀነሰ መሆኑ ተዘግቧል። በብሪታንያ ግን በትንናትናው እለት ብቻ ኮሮና ከ600 በላይ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። በኮሮና ተህዋሲ የተያዙት የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ትናንት ማምሻውን ሆስፒታል ገብተዋል።

https://p.dw.com/p/3aYRX
Britain's Prime Minister Boris Johnson PK
ምስል Reuters/M. Dunham

ኮሮና በብሪታንያ ፤የቦሪስ ጆንሰን የጤና ይዞታ

በዓለማችን በኮሮና ወረርሽኝ  የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1.2 ሚሊዮን ሲልቅ የሞቱት  ቁጥር ደግሞ ወደ 70 ሺህ መጠጋቱን የዩናይትድ ስቴትሱ የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ  ዛሬ አስታውቋል። ሆኖም በሽታው ብዙ ሰዎችን በገደላባቸው ስፓኝ ኢጣልያ እና ፈረንሳይን በመሳሰሉ ሃገራት ባለፉት  ቀናት በበሽታው የሞቱና የሚያዙትና ቁጥር እየቀነሰ መሆኑ ተዘግቧል።ኮቪድ 19 ክፉኛ በተዛመተባት በብሪታንያ ግን በትንናትናው እለት ብቻ ኮሮና ከ600 በላይ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። እስካሁን በኮሮና ወረርሽኝ ብሪታንያ ያጣችው ህዝብ ከ4943 በልጧል። በበሽታው የተያዙት ቁጥር ደግሞ ከ40 ሺህ ይልቃል። ከ10 ቀናት በፊት በኮሮና ተህዋሲ መያዛቸውን ይፋ ያደረጉት የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ትናንት ማምሻውን ሆስፒታል ገብተዋል።የብሪታንያዋ ንግሥት ኤልሳቤጥም ህዝቡ በቤቱ ተወስኖ ራሱን ከበሽታው እንዲጠብቅ ትናንት መልዕክት አስተላልፈዋል። በብሪታንያ ያለውን ሁኔታ እንዲነግረን የለንደኑን ወኪላችንን ድልነሳ ጌታነህ ስቱድዮ ከመግባቱ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ድልነሳው ጌታነህ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ