ኢትዮጵያውያን እሥረኞች በኬንያ
ዓርብ፣ ግንቦት 17 2010ማስታወቂያ
ኬንያ ውስጥ የታሰሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እስረኞቹ የሚገኙበትን ቦታ እና የታሰሩበትን ምክንያት እያጣራ መሆኑን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ። ዶይቼቬለ ያነጋገራቸው የኤምባሲው ባልደረባ የማጣራቱ ሥራ እየተገባደደ መሆኑን ገልጸው እሥረኞቹም ተፈተው በቅርቡ ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ ብለዋል። እሥረኞቹ የሚለቀቁት በቅርቡ ኬንያን የጎበኙት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ኬንያ በግዛትዋ ያሉ ኢትዮጵያውያን እሥረኞችን እንድትፈታ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት መሆኑን ተገልጿል። ከናይሮቢ ዝርዝር ዘገባ አለን