1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሳይንስ

ከፕላስቲክ ውጋጆች የጫማ ቀለም የሰራው ወጣት 

ረቡዕ፣ ጥር 20 2012

«በየጥጋጥጉ የተጣሉ የፕላስቲክ ውጋጆችን ስሰበስብ ብዙዎች ይስቁብኝ ፣ አንዳንዶች ደግሞ እንደወፈፌ ይቆጥሩኝ ነበር » ይላል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት የምህንድስና ተማሪው ልመነህ ሙላት።

https://p.dw.com/p/3WzSZ
Äthiopien Limenih Mulat
ምስል DW/S. Wegayehu

ከፕላስቲክ ውጋጆች የጫማ ቀለም የሰራው ወጣት 

«በየጥጋጥጉ የተጣሉ የፕላስቲክ ውጋጆችን ስሰበስብ ብዙዎች ይስቁብኝ ፣ አንዳንዶች ደግሞ እንደወፈፌ ይቆጥሩኝ ነበር » ይላል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት የምህንድስና ተማሪው ልመነህ ሙላት።

ያገለግሉ የፕላስቲክ ዕቃዎች ተመልሰው በጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማድረግ ያደረኩት ጥረት መና አልቀረም የሚለው ተማሪ ልመንህ ይህ ልፋቱ ዛሬ ላይ የተለየያዩ ሽልማቶችንና የፈጠራ ባለቤትነት እውቅናን እንዳተረፈለት ይናገራል ። ተማሪ ልመነህ እንደሚለው ለፈጠራ ስራ ባለቤትነት የበቃው በውሃ ኮዳነትና በእቃ መያዣነት ያገለገሉ የፕላስቲክ ውጤቶችን በመጠቀም ግሪስ በመባል የሚታወቀውን የብረት ማለስለሻ ቅባትና የጫማ ቀለም ማምረት በመቻሉ ነው ። 

ሙሉ ዘገባውን ማስፈንጠሪያውን በመጫን ያድምጡ 
ሸዋንግዛው ወጋየሁ

እሸቴ በቀለ