1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከፍተኛ ኒሻን ለባዮንቴክ ክትባት ሳይንቲስቶች

ዓርብ፣ መጋቢት 10 2013

ኮሮና ተኅዋሲን ለመከላከል ባዮንቴክ የተባለ የኮሮና መከላከያ የክትባትን ላገኙ ባል እና ሚስት ጀርመናዉያን ሳይንቲስቶች የሃገሪቱን የክብር ኒሻን አገኙ። ሁለቱ የህክምና መድሃኒት ተመራማሪዎች ዛሬ ከጀርመኑ ፕሬዚደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር ታላቅ አስተዋፅኦን ላበረከቱ የሚሰጠዉን የጀርመንን የልዩ አገልግሎት ከፍተኛ ኒሻን ተቀብለዋል። 

https://p.dw.com/p/3qt7k
Deutschland Verleihung Bundesverdienstkreuz durch Bundespräsident Steinmeier an Ozlem Tureci und Ugur Sahin
ምስል Odd Andersen/AFP/Getty Images

ኮሮና ተኅዋሲን ለመከላከል በሚደረግ ጥረት ባዮንቴክ የተባለ የኮሮና መከላከያ የክትባትን ላገኙ ባልናሚስት ጀርመናዉያን ሳይንቲስቶች የሃገሪቱን የክብር ኒሻን አገኙ። ኡር ሻሒን እና ዑዝለም ቱረቺ የተባሉት ጀርመናዉያን ሳይንቲስቶች፤ ባዮንቴክ የተባለዉን ክትባት መድሐኒት ሲያገኙ ፤ ክትባቱ ኮቪድ-19 ለመከላከል ብቻ ሳይሆን፤  በብሪታንያ እና በደቡብ አፍሪቃ የተገኘዉን ልዉጥ የተባለዉን የኮሮና ተኅዋሲ ለመከላከል የሚረዳ ሳይሆን እንዳልቀረ ተነግሮአል። ሁለቱ የህክምና መድሃኒት ተመራማሪዎች ዛሬ ከጀርመኑ ፕሬዚደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር ታላቅ አስተዋፅኦን ላበረከቱ የሚሰጠዉን የጀርመንን የልዩ አገልግሎት ከፍተኛ ኒሻን ተቀብለዋል። 
«ባለፈዉ ዓመት በጀርመን የኮሮና ተኅዋሲ እንዲህ እንደ አሁኑ የከፋ ደረጃ ሳይደርስ ተኅዋሲዉ፤  ገና ውሃን ቻይና እንደታየ ሁለቱ ሳይንቲስቶች ከባልደረቦቻቸዉ ጋር ቀን ከለሊት ጥናት አድርገዉ በሽታዉን በክትባት መከላከል ይቻላል ብለዉ መከላከያ ክትባትን አግኝተዋል። በዚህም በጀርመን ሃገር የሚሰጠዉን የልዩ አገልግሎት እዉቅና፤ ከፍተኛ የመስቀል ኒሻን  ለኡር ሻሒን እና ለዑዝለም ቱረቺ አበረክታለሁ።» 
ከስደተኛ የቱርክ ቤተሰቦች የሚወለዱት ኡር ሻሒን እና ዑዝለም ቱረቺ የተባሉት ባልናሚስት ሳይንቲቶች ለነቀርሳ መከላከያ መድሃኒት ለማግኘት ለብዙ ዓመታት ምርምር ላይ እንደነበሩ ተመልክቶአል። ባዮንቲክ የተባለዉ ኩባንያቸዉ በተለይ ኮቪድ በሽታን ለመከላከል ባደረገዉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ቀደም ሲል ከጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል የእዉቅና ሽልማት አግኝተዉ እንደነበርም የሚታወስ ነዉ። 

 

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ