1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከግለሰቦች ሹመት ባሻገር የፍትህ ስረዓቱ ከገባበት ችግር እንዴት ይውጣ?

እሑድ፣ ጥር 21 2015

ህዝቡ ያለፉትን 4 ዓመታት ስለፍትህ ብዙ ጮኋል። ፍርድቤቶች አቅም አልባ ሆነው የሚሰጧቸው ትዕዛዛት ተቀባይነት ሲያጡ በተደጋጋሚ ተስተውለዋል። የአቅም ማነስ እና የተደራጀ ሙስና የፍርድ ቤቶች መገለጫ እስከመሆን ደርሷል። ለዚህም አንዱ ማሳያ ጠቅላይ ሚንስትሩ በህዝብ ተወካዮች ፊት ቀርበው በዳኞች ላይ ያቀረቡት ትችት አንዱ ነው።

https://p.dw.com/p/4MpLI
Dr. Lemma Yifrashewa, Ato Tuli Bayissa , Ato Yalelet Teshome
ምስል privat

«የፍትሕ ስረዓቱ ተቋማዊ መፍትሔ ይሻል»

ከአራት ዓመታት ለተሻገረ ጊዜ የኢትዮጵያን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሲመሩ የነበሩት የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚደንት ባለፈው ሳምንት ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለቀዋል። ፕሬዚዳንቷ ከነ ምክትላቸው በአንድ ጊዜ በፈቃዳቸው ስራቸውን መልቀቃቸው ምናልባት በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ታሪክ የመጀመሪያው ሳይሆን አይቀርም። ጠቅላይ ሚንስትሩ በምትካቸው ወዲያው ሌሎች ሰዎችን ሾመዋል። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ስራቸውን በፈቃዳቸው ለመልቀቃቸው ምክንያታቸውን አልገለጹም ። ነገር ግን ጠቅላይ ሚንስትሩ በቤተመንግስት ጋብዘዋቸው ከነምክትላቸው አመስግነው ማሰናበታቸውን ሰምተናል። «የፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ እየተከበረ አይደለም» ጠበቆችበኢትዮጵያ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚደንት ከአራት ዓመት በፊት ወደዚህ ትልቅ የኃላፊነት  ሲመጡ ብዙ ተብሎላቸው ነበር። በተለይ በአሰራር ችግር እና ሙስና ስር የሰደደባቸውን ፍርድ ቤቶች  ከላይ እስከ ታች ሊለውጡ ይችላሉ ተብሎም ተስፋ ተጥሎባቸው ነበር። ነገር ግን  የፍርድ ቤቶችን ጨምሮ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የፍትህ ስረዓቱ ከድጡ ወደ ማጡ መሆኑን የሚገልጹ ብዙኃን ናቸው ።  ህዝቡ ያለፉትን 4 ዓመታት ስለፍትህ ብዙ ጮኋል። ፍርድቤቶች አቅም አልባ ሆነው የሚሰጧቸው ትዕዛዛት በጸጥታ አካላትም ሆነ በሌሎች ተቀባይነት ሲያጡ በተደጋጋሚ ተስተውለዋል። የአቅም ማነስ እና የተደራጀ ሙስና የፍርድ ቤቶች መገለጫ እስከመሆን ደርሷል።የፍርድ ቤት ውሳኔና የፖሊስ ዳተኝነት ለዚህም አንዱ ማሳያ ጠቅላይ ሚንስትሩ በህዝብ ተወካዮች ፊት ቀርበው በዳኞች ላይ ያቀረቡት የሰላ ትችት አንዱ ነው። የፍትህ ስረዓቱ በራሱ ሀገሪቱ አሁን ለገባችበት ቀውስ የራሱን አስተዋጽዖ አበርክቷል የሚሉም አሉ። የዜጎች በሰላም ወጥተው መግባት፣ ሀብት ንብረታቸው የመጠበቅ ብሎም በሰላማዊ አካባቢ ውስጥ የመኖር ዋስትና በዚሁ የፍትህ ስረዓት ውስጥ የሚረጋገጥ እንደመሆኑ መጠን ስረዓቱ ጠንካራ እና ዘላቂነት ያለው ማሻሻያ እንደሚፈልግ በስፋት ይነገራል። አዲስ ፕሬዚዳንት ያገኘው ጠቅላይ ፍርድቤት እና የፍትህ ስረዓቱ ተጨባጭ ሁኔታ በኢትዮጵያ ደግሞ  የእንወያይ ዝግጅታችን ርዕሰ ጉዳይ ነው። በውይይታችን ዶ/ር ለማ ይፍራ ሸዋ ፣ አቶ ቱሊ ባይሳ ፣ አቶ ያለለት ተሾመ በእንግድነት ተጋብዘው ተሳትፈዋል።የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እና ማረሚያ ቤቶች 

Äthiopien Der neu ernannte Präsident Tewdros Mihret und der Vizepräsident des Obersten Gerichtshofs Abeba Embiale
አዲሶቹ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ተሻሚዎች አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና ምክትላቸው ወ/ሮ አበባ እምቢአለምስል Ethiopian Broadcasting Corporation
Äthiopien Addis Abeba | Eingang | Bundesgerichtshof
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎትምስል Seyoum Hailu/DW
Äthiopien Rücktritt Meaza Ashenafi Präsidentin des Bundesgerichtshofs und Stellvertreter Solomon Areda Waktolla
ተሰናባቾቹ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እና ምክትላቸው ወ/ር መዓዛ አሸናፊ እና አቶ ሰለሞን አረዳምስል Office Prime Minister Ethiopia

ታምራት ዲንሳ