1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከኮንሶ የተፈናቀሉ እርዳታ እየተጠባበቁ ነው

ሐሙስ፣ ኅዳር 17 2013

በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን ባለፈው ሳምንት የታጠቁ ሀይሎች አደረሱት በተባለው ጥቃትና ግጭት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች የሰብዓዊ ድጋፍ ባለማግኘታቸው መቸገራቸውን ገለጹ። ከዞኑ ሰስት ወረዳዎች ተፈናቅለው በተለያዩ ቀበሌያትና በአጎራባች ወረዳዎች ተጠልለው የሚገኙ ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለ እንዳሉት እስከአሁን ያናገራቸውም ሆነ ድጋፍ ያደረገላቸው አካል የለም።

https://p.dw.com/p/3lrws
Äthiopien Konflikt zwischen Konso & Ale
ምስል Ale Communication Office

ከኮንሶ የተፈናቀሉ እርዳታ እየተጠባበቁ ነው

በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን ባለፈው ሳምንት የታጠቁ ሀይሎች አደረሱት በተባለው ጥቃትና ግጭት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች የሰብዓዊ ድጋፍ ባለማግኘታቸው መቸገራቸውን ገለጹ።
ከዞኑ ሰስት ወረዳዎች ተፈናቅለው በተለያዩ ቀበሌያትና በአጎራባች ወረዳዎች ተጠልለው የሚገኙ ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለ እንዳሉት ከቀያቸው ከወጡ ቀናትን ቢያስቆጥሩም እስከአሁን ግን ያናገራቸውም ሆነ ድጋፍ ያደረገላቸው አካል የለም።

የኮንሶ ዞን የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት መምሪያ የስራ ሃላፊዎች በበኩላቸው ከዞኑ ለተፈናቀሉ ከ94 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የቀለብና የአልባሳት ድጋፍ እንዲቀርብ ለደቡብ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በማቅረብ ምላሽ እየጠበቁ እንዳሉ ተናግረዋል።ተፈናቅለዋል በሚል ከዞኑ የቀረበው ቁጥር የተጋነነ ነው የሚሉት የደቡብ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጋንታ ጋሞአ በበኩላቸው የተረጂዎችን ትክክለኛ ቁጥር በባለሙያዎች እየተለየ ይገኛል ብለዋል።

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 

እሸቴ በቀለ
ማንተጋፍቶት ስለሺ