1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከአዲስ አበባ ጅቡቲ የሚያመራው መንገድ ተዘግቶ ዋለ

እሑድ፣ ጥር 5 2011

ከአዲስ አበባ የአዋሽ እና የሰመራ ከተሞችን አቋርጦ ወደ ጅቡቲ የሚያመራው መንገድ ተዘግቶ ዋለ። ድሬዳዋ፣ ሐረር እና ጅግጅጋን ከዋና ከተማዋ የሚያገናኘው የመንገዱ ክፍልም በአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ ግልጋሎት አቁሞ ታይቷል።

https://p.dw.com/p/3BUSQ
Äthiopien Straße Ababa-Djibouti
ምስል DW/Y. Gebregziabher

የባቡር አገልግሎት ተቋርጦ ነበር

ከአዲስ አበባ አዋሽ እና የሰመራ ከተሞችን አቋርጦ ወደ ጅቡቲ የሚያመራው መንገድ ተዘግቶ ዋለ። ድሬዳዋ፣ ሐረር እና ጅግጅጋን ከዋና ከተማዋ የሚያገናኘው የመንገዱ ክፍልም  በአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ ግልጋሎት አቁሞ ታይቷል። የDW ዘጋቢ ዮሐንስ ገብረ እግዚዓብሔር ያነጋገራቸው እና በተቃውሞው የሚሳተፉ የአፋር ክልል ነዋሪዎች ጥያቄዎቻችን ምላሽ ሊሰጣቸው ይገባል በማለት መንገድ መዝጋታቸውን ተናግረዋል። የአፋር እና የሶማሌ ክልል በይገባኛል የሚወዛገቡባቸው አካባቢዎች ለሶማሌ ክልል ሊሰጡ ነው የሚል መረጃ ለተቃውሞ እንዳበቃቸውም ገልጸዋል።

በማኅበራዊ ድረ-ገፆች የተሰራጩ ምስሎች ከአዲስ አበባ ወደ ምሥራቁ የኢትዮጵያ ክፍል በሚያመራው መንገድ በርከት ያሉ ተሽከርካሪዎች ቆመው አሳይተዋል። የክልሉን ሰንደቅ ዓላማ የሚያውለበልቡ እና በአውራ ጎዳናው መካከል ድንኳን ጥለው ተሽከርካሪ እንዳይተላለፍ ያገዱ ነዋሪዎችም ነበሩ። ከተሽከርካሪዎች በተጨማሪ ከኢትዮጵያ ወደ ጅቡቲ የሚያመራው የባቡር አገልግሎት በተቃውሞው ሳቢያ ተቋርጧል። ዮሐንስ ገብረ እግዚዓብሔር መንገድ የዘጉ ተቃዋሚዎችን ለምን ሲል ጠይቋቸዋል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚዓብሔር
እሸቴ በቀለ