1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከአዲሱ የኢትዮጵያ መንግስት የሚጠበቀዉ ዲፕሎማሲ 

ማክሰኞ፣ መስከረም 25 2014

የአፍሪቃ ሐገራት መሪዎች  የኢትዮጵያን ታላቅ ሐገርነት መስክረው፣ሐገሪቱ አሁን የገጠማትን የሠላም እና የአንድነት ጥያቄዎችን መፍታት የተመራጩ ጠቅላይ ሚኒስትር ቀጣይ የቤት ስራ መሆኑን አስረድተዋል

https://p.dw.com/p/41IMK
Äthiopien | PM Abiy Einweihungszeremonie in Addis Abeba
ምስል Solomon Muche/DW

የኢትዮጵያ የወደፊት ዲፕሎማሲ እንዴትነት

ትናንት አዲስ አበባ ዉስጥ በተከበረዉ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ በዓለ ሲመት ላይ የተገኙ የአፍሪቃ ሐገራት መሪዎች  የኢትዮጵያን ታላቅ ሐገርነት መስክረው፣ሐገሪቱ አሁን የገጠማትን የሠላም እና የአንድነት ጥያቄዎችን መፍታት የተመራጩ ጠቅላይ ሚኒስትር ቀጣይ የቤት ስራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡በበዓለ ሲመቱ ላይ በጉሉሕ የሚጠቀሱ የምዕራባዉያን ሐገራት ተወካዮች አለመገኘታቸዉ የዐብይ መንግሥት ከምዕባዉያን ጋር ያለዉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሻከሩን ጠቋሚ እንደሆነ እየተነገረ ነዉ።

 ስዩም ጌቱ 

ነጋሽ መሐመድ 

ሸዋዬ ለገሰ