1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከአቶ አባዱላ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

ሐሙስ፣ ኅዳር 10 2013

ሰሞኑን የፌዴራል መንግስት "ህወሃት ላይ ያነጣጠረ ነው" በሚል በትግራይ ክልል እየወሰደ ላለው የውጊያ አማራጭ ተጠያቂው እራሱ ህወሓት ነው አሉ የቀድሞው የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣን አቶ አባዱላ ገመዳ፡፡

https://p.dw.com/p/3lZfT
Äthiopien Verteidigungsminister Abadula Gemeda  Addis Abeba
ምስል Seyoum Getu/DW

«የሁለቱ ወገኖች ልዩነት የመጥበብ አዝማሚያን አላሳየም»

ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በተለያዩ የሃገሪቱ ከፍተኛ የስልጣን እርከኖች ላይ ሲሰሩ የነበሩት አቶ አባዱላ ገመዳ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ በፌዴራሉ እና ትግራይ ክልልን በሚያስተዳድረው "ህወሓት" መካከል የነበሩ የሃሳብ ልዩነቶች ጦር ለመማዘዝም የማያበቁ እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡ ይሁንና ከብልጽግና ፓርቲ ምስረታ በኋላ "የሁለቱ ወገኖች ልዩነት የመጥበብ አዝማሚያን አላሳየም" ያሉት የቀድሞው ጉምቱ ባለስልጣን በተለይም ህወሓት "በፌዴራሉ መንግስትና በህገመንግስቱም ጭምር እውቅና የተነፈገ" ካሉት የትግራዩ ምርጫ በኋላ ግን ነገሮች ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ማምራታቸውን እና የድርድር መስመርን ያጠበቡ ብለውታል፡፡ በህወሓት ባለስልጣንም ጭምር ተረጋግጧል ያሉት የሰሜን ዕዝ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የተወሰደው ያልታሰበ ያሉት ጥቃት ደግሞ "የፌዴራሉ መንግስት ተገዶ ወደ ጦርነት ለመግባቱ ማሳያ ነው" ያሉት አቶ አባዱላ አሁን ሊደርስ የሚችለውን ቀውስ የሚያሳንሰው የጦርነቱን ጊዜ ማሳጠር ብቻ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡


ስዩም ጌቱ 
ኂሩት መለሰ