1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከትግራይ ተወላጆች ማኀበር የቀረበ የሰላማዊ መፍትሄ

ዓርብ፣ ጥር 6 2014

ደሕንነት እና ፍትሕ ለትግራይ የተሰኘው በአሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ማኀበር በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማቆም የሰላማዊ መፍትሄ ጥሪ አቀረበ። የማኀበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት እንደገለጹት ማኀበሩ ጥሪውን ያቀረበው ለአፍሪካ ህብረትና ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት በፃፈው ግልጽ ደብዳቤ ነው።

https://p.dw.com/p/45XLy
Äthiopien SJT Logo

ግልጽ ደብዳቤ ለአፍሪቃ ህብረትና ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት

ደሕንነት እና ፍትሕ ለትግራይ የተሰኘው በአሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ማኀበር በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማቆም የሰላማዊ መፍትሄ ጥሪ አቀረበ። የማኀበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት ኘሮፌሰር ሙሉጌታ ገብረእግዚአብሄር ለዶይቸ ቬለ እንደገለጹት ማኀበሩ ጥሪውን ያቀረበው ለአፍሪቃ ህብረትና ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት በፃፈው ግልጽ ደብዳቤ ነው። ስለጉዳዩ አስተያየት የሰጡን በፊኒክስ አሪዞና ነዋሪና የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ የሚከታተሉት ዶክተር ገበየሁ እጅጉ በበኩላቸው ሰላም አስፈላጊ ቢሆንም ህወሓት ሰላም ፈላጊ ድርጅት አይደለም ብለዋል።

 

ታሪኩ ኃይሉ

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ