ከቤኒሻንጉል ተፈናቅለው ባሕር ዳር የተጠለሉ ዕርዳታ አላገኘንም አሉ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 10 2011ማስታወቂያ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማሺ ዞን በተቀሰቀሰ ግጭት ተፈናቅለው ባሕር ዳር የተጠለሉ ዜጎች ዕርዳታ አላገኘንም አሉ። ተፈናቃዮቹ በከማሺ ዞን ከሚገኘው ቀያቸው እስከ ባሕር ዳር ሲጓዙ በርካታ ፈተና እንደገጠማቸው ተናግረዋል። የአማራ ክልል በበኩሉ አቅሙ የፈቀደውን ያክል እርዳታ እያቀረበ መሆኑን ገልጿል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተዘጋው መንገድ ሲከፈት እና ጸጥታው ሲረጋጋ ወደ ቀያቸው እንደሚመለሱ አስታውቋል። ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ከመስከረም 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በተከሰተው ግጭት ከ45 ሺሕ በላይ ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን 670 ዎቹ በባሕር ዳር ከተማ ይገኛሉ።
ዓለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ