ከሳውዲ የሚወጣ ገንዘብ
ማክሰኞ፣ ጥር 16 2009ማስታወቂያ
የሳውዲ አረብያ መንግሥት የውጭ ዜጎች ወደ ሀገራቸው ገንዘብ ሲልኩ ቀረጥ እንዲጣልባቸው የቀረበለትን ሀሳብ ተግባራዊ እንደማያደርግ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አስታወቀ ። ሹራ የተባለው የዘውዳዊው ስርዓት አማካሪ ምክር ቤት የውጭ ዜጎች ወደ ሀገራቸው በሚልኩት ገንዘብ ላይ 6 በመቶ ቀረጥ እንዲከፍሉ ባለፈው ዓመት ሀሳብ አቅርቦ ነበር ። ይሁንና የሀገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ባለፈው እሁድ በትዊተር ባሰራጨው መልዕክት ሳውዲ አረብያ ወደ ሀገርዋ በሚገባ እና በሚወጣ ገንዘብ ነጻ ዝውውር እንደምትጸና አስታውቋል ። በጉዳዩ ላይ የሪያዱን ወኪላችንን ስለሺ ሽብሩን ቀደም ሲል በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
ስለሺ ሽብሩ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ