1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከሰሞኑ ጥቃት አስቀድሞ ምልክቶች እንደነበሩ ጥናት አመለከተ

ማክሰኞ፣ መስከረም 8 2011

በአዲስ አበባና አካባቢዋ እየተከሰቱ ያሉት ሁከቶችና ብሔር ተኮር ጥቃቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ቀደም ብሎ ምልክቶች መታየታቸውን አንድ የዳሰሳ ጥናት አመለከተ። ጥናቱን ያደረጉት የስነ ማህበረሰብና የህግ ባለሙያ በፀጥታ ኃይሉ ቸልተኝነትና ቀድሞ ዝግጅት አለማድረግ ምክንያት ሰዎች እየሞቱ እና ጉዳት እየደረሰባቸው እንዳለ አብራርተዋል።

https://p.dw.com/p/357ET
Äthiopien Proteste in Addis Abeba
ምስል picture-alliance/AA/M.W. Hailu

ከሰሞኑ ጥቃት አስቀድሞ ምልክቶች እንደነበሩ ጥናት አመለከተ

ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ እየተከሰቱ ባሉ ሁከቶች እና ብሔር ተኮር ጥቃቶች የሞት፣ የአካል መጉደል፣ የንብረት ውድመት እና ከይዞታ መፈናቀል የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ህይወት እያመሰው ይገኛል። እነዚህን ችግሮች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ምልክቶች አስቀድመው መታየታቸውን የስነ ማህበረሰብና የህግ ባለሙያው አቶ ተስፋዬ ደገፋ ለDW ተናግረዋል።

የአርበኞች ግንቦት 7 ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ ከመግባቱ አስቀድሞ በነበሩት ቀናት የአውራ ጎዳናዎች፣ አደባባዮች፣ የህዝብ መገልገያ ተቋማት እና የአገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን ለማሸብረቅ ቀለም ሲቀባ የህግ አስከባሪ አካላት በዝምታ መመልከታቸው ለችግሩ አንድ ግብዓት መሆኑን የዳሰሳ ጥናታቸውን ተመርኩዘው ባለሙያው ያስረዳሉ። 

ዝርዝር ዘገባውን የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።  

ዳግማዊ ሲሳይ
ተስፋለም ወልደየስ

 
ነጋሽ መሐመድ