1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሞያሌ ተፈናቃዮች

ዓርብ፣ መጋቢት 21 2010

ከተፈናቃዮቹ መካከል ዋስትና ክልተሰጠን አንመለስም ያሉም እንዳሉም ተነግሯል። ከዚህ ሌላ እዚያው ኬንያ በርካታ ተፈናቃዮች የፖለቲካ ጥገኝነት እንዲሰጣቸው ሲመዘገቡ መሰንበታቸው ተነግሯል። ከመካከላቸው ወደ ሃገራቸው የተመለሱ አሉም ተብሏል።

https://p.dw.com/p/2vFkr
Äthiopien vertriebene Moyale-Bewohner in der Oromia-Region
ምስል privat

የሞያሌ ተፈናቃዮች

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ሞያሌ ውስጥ የመከላከያ ሠራዊት የፈፀመውን ጥቃት ሸሽተው ኬንያ የተሰደዱት ኢትዮጵያውያን ወደ ቀያቸው እየተመለሱ መሆኑን የዓይን እማኞች ተናግረዋል። ሌሎችም ዶክተር አብይ አህመድ በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንደሚመረጡ ከሰሙ በኋላ ለመመለስ እየተዘጋጁ መሆኑንም ገልፀዋል። ከተፈናቃዮቹ መካከል ዋስትና ክልተሰጠን አንመለስም ያሉም እንዳሉም ተነግሯል። የዓይን ምስክሮቹ ስለስደተኛው መመለስ የሰጡት አስተያየት የተመ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅትም ሆነ የኬንያ ቀይ መስቀል ባለሥልጣናት አላረጋገጡም።  ከዚህ ሌላ እዚያው ኬንያ በርካታ ተፈናቃዮች የፖለቲካ ጥገኝነት እንዲሰጣቸው ሲመዘገቡ መሰንበታቸው ተነግሯል። ከመካከላቸው ወደ ሃገራቸው የተመለሱም አሉ መባሉን ቻላቸው ታደሰ ከናይሮቢ ዘግቧል። 
ቻላቸው ታደሰ 
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ