1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከመጋረጃው ጀርባ

እሑድ፣ ታኅሣሥ 7 2011

''ተውኔትን በተውኔት ውስት የምንመከትበት የአፃፃፍ ስልት ተከትኮ የፃፈው ተውኔት ነው። በጊዜው ለመድፈር የሚዳዳን ሀሳብ በደንብ የህዝቡን ትርታ ተንፍሷል።'' ትያትሩ የመድረክ ቆይታው 2:30 ሁለት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ ያህል ይታያል። በሀገር ፍቅር ቴያትር በየሳምንቱ መጨረሻ እሁድ ይቀርባል። 

https://p.dw.com/p/3AD5U
Äthiopien Addis Ababa - Kemegarejaw Jerba Theater
ምስል Tofik Nuri

ከመጋረጃው ጀርባ ቴያትር

''የታመሙ እናት አሉ። ሁሉም ልጆች ከእኔ በላይ ለእናቴ የሚያውቅ የለም'' ይላሉ ከመጋረጃው ጀርባ ተውኔት። ብር አንባር የመጀመሪያ ትያትሩ ሲሆን ከመጋረጃ ጀርባ ለመድረክ ሲያበቃ ሁለተኛው ነው። ከመጋረጃው ጀርባ ቴያትር ደራሲ ቶፊቅ ኑሪ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴያትር መምህር ነው። ከዘጠኝ ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ይታዩ የነበሩት ብሄር ተኮር ግጭቶች፤ ያስከፉኝ ነበር ይላል። የኢኮኖሚክስ ትምህርቱን ይማር በነበረበት የመቀሌ ዩኒበርስቲም ሆነ በሌላውም የሀገሪቱ ዩኒበርስቲዎች ይነሳ የነበረው ብሄርን ትኩረት አድርጎ ግጭቶች ይቀሰቀሳሉ። በሀሳብ ሲብሰለሰል የቆየው ቶፊቅ የቴያትር ትምህርቱን ሲጀምር በውስጡ ሲመላለስ የነበረውን የብሄር ልዩነት ግጭቱን በተውኔት መልክ በክፍል ውስጥ አቀረበ፤ መልካም ምላሽም አገኘ። ተውኔቱን አዳብሮ ጽፎ በ2005 ዓ.ም ለህዝብ እይታ እንዲቀርብ ለቴያትር ቤት አቀረበ። ከሁለት ዓመታት ቆይታ በሃላ ተሳካለት። ትያትሩ ለመድረክ ከመቅረቡ በፊት ሁለት ዓመታት ዝግጅት ተደርጎበታል። በሀገር ፍቅር ቴያትር ታህሳስ 10 ቀን 2010 ዓ.ም ለመድረክ መታየት በቃ። በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የሚያጠነጥን ሆኖ የአንድ እናት ልጆች መሆናችንን የሚያሳይ ቴያትር ነው ይላል ከመጋረጃው ጀርባ ደራሲ ቶፊቅ ኑሪ።''ትያትሩ የኢትዮጵያ አንድነት ላይ የሚያጠነጥን ነው። የአንድ እናት ልጆች መሆናችንን የሚያሳይ የጥበብን ጉልበት ተጠቅመን አዎንታዊ ሚና ለመጫወት የተሰራ ነው።'' ይገረም ደጀኔ /አስቴር/ ከመጋረጃው ጀርባ በትወና ተሳትፏል። ይገረም ትያትሩን ሁለት ነገሮች ልዩ ያደርገዋል ሲል፤ የሀገራችንን ችግር መሰረት አድርጎ የተሰራ መሆኑንም ያስረግጣል፤ ወቅታዊና ሀገራዊ አጀንዳን በማንሳት ተዋናያኖችን ወክሎ የተሰራ ቴያትር ነው ይለናል። በመጋረጃ ፊትና በመጋረጃ ጀርባ የተሰራ ቴያትር እንደመሆኑ ሰባት የነበሩት በመድረኩ የምናያቸው ገፀ ባህሪያት 14 ሆነው እናገኛቸዋለን። በዚህም የተውኔቱን ገፀ ባህሪያት ሲጫወት ትንሽ ከበድ ብሎኛል ይላል ይገረም። ''በልዩነቱ ውስጥ አንድነት ሊያኖረን እንጂ በመጣላት በመጨቃጨቅ በፀቡ በጦርነቱ በመገዳደሉ ማንም ተጠቃሚ አይደለም''አርቲስት ተስፋአለም ታምራትም ለየት የሚል ተውኔት ነው ሲል እንዲህ ይገልጻል። ''እያዝናና ትልቅ ሀገራዊ ጉዳይ ይዞ የሚያስተምር ነው'' አቶ ቻላቸው ፈረጅ በአዲስ አበባ ዩኒበርስቲ የቴያትር ጥበባት ትምህርት ቤት መምህር ናቸው። ከመጋረጃው ጀርባ ቴያትር ለየት ባለ መልኩ እንደቀረበ ገልጸውልናን፤ ተውኔትን በተውኔት የአጻጻፍ ስልትን ተከትሏልም ይላሉ።''ተውኔትን በተውኔት ውስት የምንመከትበት የአፃፃፍ ስልት ተከትኮ የፃፈው ተውኔት ነው። በጊዜው ለመድፈር የሚዳዳን ሀሳብ በደንብ የህዝቡን ትርታ ተንፍሷል።'' ትያትሩ የመድረክ ቆይታው 2:30 ሁለት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ ያህል ይታያል። በሀገር ፍቅር ቴያትር በየሳምንቱ መጨረሻ እሁድ ይቀርባል። 


ነጃት ኢብራሂም 
ልደት አበበ