1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦፌኮ እና ኦነግ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

ሰኞ፣ ጳጉሜን 5 2010

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን አስታወቁ። ሁለቱ ፓርቲዎች የኦሮሞ ሕዝብ ድምፅ እንዳይከፋፈል በጋራ ለመሥራት መስማማታቸውን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/34dlI
Äthiopien Proteste | Mulatu Gamachu
ምስል DW/M. Yonas Bula

Q&A with Mulatu Gemechu - MP3-Stereo

የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን አስታወቁ። የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ እንደተናገሩት ሁለቱ ፓርቲዎች የኦሮሞ ሕዝብ ድምፅ እንዳይከፋፈል በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል። መቀመጫውን በኤርትራ አድርጎ የነበረው እና በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ መወሰኑን አስታውቋል። የኦነግ መሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ በመጪው መስከረም 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

 እሸቴ በቀለ 

ኂሩት መለሰ