1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦፌኮ ሌላ ምርጫ እንዲካሄድ ጠየቀ

ዓርብ፣ ሰኔ 18 2013

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ኢትዮጵያ ሰሞኑን ያካሄደችውን ምርጫ «በብሔራዊ መግባባት ያልታጀበ» እና «የአገሪቱን ውስብስብ ችሮች የማይፈታ ነው» ነው አለ። በአንድ ዓመት ውስጥ ሁሉን አቀፍ ነፃ ምርጫ እንዲካሄድም በዚሁ መግለጫው ጠይቋል።

https://p.dw.com/p/3vYnI
Pro Merera Gudina vorsitzender OFECO
ምስል DW/S. Wegayehu

«ፍትሓዊና አካታች ያልሆነ ምርጫ ዴሞክራሲን አያዋልድም»

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ኢትዮጵያ ሰሞኑን ያካሄደችውን ምርጫ «በብሔራዊ መግባባት ያልታጀበ» እና «የአገሪቱን ውስብስብ ችሮች የማይፈታ ነው» ነው አለ። ፓርቲው ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳለው «በአንድ ፓርቲ የበላይነት የተጠመደው» ያለውን ገዥውን ፓርቲም «ለፖለቲካ ድርድር ያልተዘጋጀ» በሚልም ወቅሷል። ኦፌኮ በአንድ ዓመት ውስጥ ሁሉን አቀፍ ነፃ ምርጫ እንዲካሄድም በዚሁ መግለጫው ጠይቋል። የብልጽግና ፓርቲ ቃል አቀባይ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ ግን ይህን የኦፌኮን አቋም ነቅፈው በሰጡት ምላሽ  ምርጫው «ነጻና አሳታፊ» ነበር፤ በኦሮሚያም ከአስር ፓርቲዎች በላይ በምርጫው በመሳተፍ ተፎካክረዋልም ብለዋል።

ስዩም ጌቱ 

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ