ኢትዮጵያን የመታዉ ድርቅ መዘዝ ቀጥሎአል
ማክሰኞ፣ ኅዳር 13 2009መንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ የርዳታ ድርጅቶች ይኸው አሳሳቢ ሁኔታ ወደከፋ የሰብዓዊ ቀውስ እንዳይቀየር ምን እየሰሩ ነዉ? መርጋ ዮናስ ዘገባ አለዉ።
በኢትዮጵያ በሃምሳ ዓመት ዉስጥ የመጀመርያ የተባለዉ አስከፊ ድርቅ በመከሰቱ ከ10 ሚልዮን ሰዎች በላይ መጠቃታቸዉ ይታወሳል። በዚያም ላይ ተደርቦ በግንቦትና በሰኔ ወሮች ዉስጥ ሃይለኛ ጎርፍ ባስከተለዉ አደጋ 600,000 በላይ ሰዎች ከቄያቸው መፈናቀላቸው የተመድ የሰባዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ቢሮ «OCHA» በግዜዉ ዘግቦት ነበር። ተቋሙ ትላንትና ባወጣዉ ዘገባ ከድርቁና ከጎርፉ ጋር ተዳምሮ የተከሰቱት የጤና ችግሮችና ሌሎች መሰረታዊ የማኅበረሰብ አገልግሎቶች መናወጡ አሁንም የ9,7 ሚልዮን ሰዎች ሕይወት ላይ አሉታዊ ተፅኖ ማስቀጠሉን አመልክተዋል።
10,2 ሚልዮን የነበረዉ የተረጅዎች ቁጥር ወደ 9,7 መዉረዱን የሚናገሩት በኢትዮጵያ በብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደበበ ዘዉዴ አሁን ያሉት የተረጅዎች ቁጥር በመንግስትና በ«OCHA» ተከፋፍለዉ ርዳታ እየተደረገላቸዉ መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ በሚገኘዉ ከሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ቢሮ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ኢየሰሩ እንደሆነ ለማወቅ ባቀርብነዉ ጥያቄ፣ የሃገሪቱን የሰብዓዊ ጉዳይ የሚከታተለዉ ቡድን የመርህ ግዜ ግምገማ እያደረጉ እንደሚገኙና ቡድኑ ሲመለስ መረጃ ለመስጠት ዝግጁ እንደሆነ በላኩልን የኢሜል መልክት ገልፀዉልናል። ይሁን እንጅ ይሄ የመኸር ግምገማ ምን እንደሆነ አቶ ደበበ አብራርተዋል።
በኢትዮጵያ አዲስ ድርቅ ሊከሰት እንደሆነ ባላፈዉ ሳምንት «OCHA» መግለፁም ይታወቃል። የኢትዮጵያ መንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ የርዳታ ድርጅቶች በዚህ ላይ ምን እየሰሩ ነዉ ለሚለዉ ጥያቄ አቶ ደበበ መልስ ሰጥተዋል።
በሶማሌ ክልል የምገኙ 60 ቀበሌዎችን ጨምሮ አፋር፣በኦሮሚያ፣ በትግራይና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ከፍተኛ የዉኃ እጥረት መከሰቱን «OCHA» በዘገባዉ አመልክተዋል። የሃገሪቱ የሜትርዮሎጂ ኤጀንሲም የሰብዓዊ ችግሩ አስከፊነት እንዳይባባስ ለማድረግ ገበሬዎች የመኽር ግዜ ሰብል ቶሎ ብሎ መሰብሰብ እንዲጀምሩ አሳስበዋል።
መርጋ ዮናስ
አዜብ ታደሰ