1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦባ ኤውአሬ

Sam Olukoya
ሐሙስ፣ ሰኔ 18 2012

የቀድሞው የቤኒን ሥርወ መንግሥት ንጉስ ኦባ ኤውአሬ ትተውት ያለፉት ቅርስ ያስተዳድሩ ከነበረበት አምስት ምዕተ ዓመታት በኋላም የሚታይ ነው። ሌላው ደግሞ የሥርወ መንግሥቱ ተተኪዎች ከዚህ በፊት ይካሄድ በነበረው መልኩ በኃይል ሳይሆን በሰላም እና ዘላቂነት ባለው መልኩ እንዲከናወን እኝህ ሰው ትልቅ ሚና ተጫውተዋል።

https://p.dw.com/p/3eG2z
African Roots | Oba Ewuare 1 | Porträt
African Roots | Oba Ewuare 6

ኦባ ኤውአሬ፦ የቤኒን ሲቲ የነሀስ ንጉስ

ኦባ ኤውአሬ መቼ ኖሩ?
ኦባ ኤውአሬ ፤ ቀዳማዊ ኦባ ኤውአሬ ወይም ታላቁ አባ ኤውአሬ በመባል ይታወቃሉ። እሳቸውም ጥንታዊውን የቤኒን ሥርወ መንግሥት ከ 1440 እስከ 1473 ድረስ መርተዋል። የቤኒን ኦባ የሆኑት እና ስልጣኑን የጨበጡት የገዛ ወንድማቸውን ኡዋይፊኦኩምን በኃይል ካስወገዱ በኋላ ነው።በመፈንቅለ መንግስቱ ከተማይቱ የቤኒን ሲቲ  ፈራርሳ ነበር ነገር ግን እንደገና ገንብተዋት ከምዕራብ አፍሪቃ ታዋቂ እና ከታላላቅ ግዛቶች አንዷ እንድትሆን አድርገዋል።
ኦባ ኤውአሬ አገዛዝ ምን ይመስል ነበር?
በኤውአሬ የግዛት ዘመን የቤኒን ዋና ከተማ በጥሩ ሁኔታ የተደራጀችና እና ብዙ ሰዎች እንዲተዳደሩባት የተሰናዳች ነበር። እሳቸውም ወደ ቤኒን የሚያስገቡ ዘጠኝ በሮች እንዳስገነቡ እና የበርካታ መንገዶች ግንባታን ይቆጣጠሩ እንደነበር ይነገራል።በስነ ቃል እንደሚነገረው ከሆነ ደግሞ ኤውአሬ ጥበበኛ ፣አስማተኛ ፣ ዶክተር እና ተዋጊ ነበሩ። 
የቤኒን ኦባ ኤውአሬ  በምን የጥበብ ስራዎች ይታወቃሉ?
ከኦባ ኤውአሬ  ቅርሶች አንዱ የቤኒንን ሥነ ጥበብ ማፋፋት ነው። የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችን ወደ ከተማዋ በመጋበዝ ጥራት ያላቸውን የጥበብ ሥራዎች እንዲመረቱ አበረታተዋል። በተጨማሪም የሞቱትን የቤኒን ነገሥታትን ለማስታወስ ከነሐስ የተሰሩ እና ከአንገት በላይ የሆኑ ሀውልቶችን አሰርተዋል። እነዚህ የጥበብ ስራዎች በናይጄሪያ እና በዓለም ዙሪያ ሙዚየሞች እጅግ ታሪካዊ የሆኑ ሥራዎች ናቸው። ኤውአሬ ሥነ ጥበብ እንዲበረታታ ያደረጉት ድጋፍ በዝሆን ጥርስ ፣ በእንጨት እና በነሀስ ስራዎች የሚታወቅ ስኬታማ የስነጥበብ ኢንዱስትሪ እንዲቋቋም ምክንያት ሆኗል ።
በኦባ ኤውአሬ ዘመነ ግዛት ባህል እንዴት ዳበረ? 
ኦባ ኤውአሬ የቤኒን ባህላዊ እንቅስቃሴዎች በማስተዋወቅ ይታወቃሉ። ቤኒን ውስጥ ካስተዋወቁት ዝነኛው እና እጅግ ወሳኝ ባህላዊ ክስተቶች አንዱ  እስከዛሬ ድረስ  የዘለቀውና በቤኒን ህዝብ ትልቅ ስፍራ  የሚሰጠው የኢጂን ፌስቲቫል ነው። ሌላው ኦባ ኤውአሬ ያስተዋወቁት በቀለማት ያሸበረቁ የኮራል ዶቃዎች ናቸው። ዛሬ የቤኒን ባህላዊ አለባበስ እና ለንጉሣዊ ጌጣጌጦች  አስፈላጊ ገጽታዎች ናቸው። ዛሬ የኮራል ዶቃዎች በቤኒን ብቻ አልተወሰኑም። ለኦባ ኤውአሬ ምስጋና ይግባቸውና በደቡብ ናይጄሪያ በብዙ አካባቢዎች በስፋት ይገኛሉ።
የኦባ ኤውአሬ ሌሎች ስኬቶች ምንድን ናቸው?
ታላቁ ኤውአሬ ብዙውን ጊዜ የመጀመሪያው የቤኒን ኦባ የሚባሉት የቤኒን ሥርወ መንግሥት የመጀመሪያው መሪ ስለሆኑ ሳይሆን ፣ በስልጣናቸው ፍሬያማ ነገር የሰሩ የመጀመሪያው ንጉሥ ስለሆኑ ነው። የወረሱትን ትንሽ ግዛት በርካታ ከተሞችን እና መንደሮችን በማካተት አስፋፍተዋል። በመንግሥቱ ውስጥ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር እንዲኖር ያደረጉት የአስተዳደር ለውጥ እስከዛሬ ድረስ ያለ ቅርስ ነው።  ስልጣንን ከአባት ወደ ቀዳሚው ወንድ ልጅ በማሸጋገር የቀድሞ ዘመን ኃያላን ነገሥታት ትግል እንዲያከትም አድርጓል።

ኦባ ኤውአሬ

ይህ ዘገባ አፍሪካዊ ሥረ-መሠረት በሚል ከጌርዳ ሔንክል ተቋም ጋር በመተባበር የሚቀርብ ዝግጅት ነው። የዘገባው ሳይንሳዊ ምክር የተገኘው ከፕሮፌሰር ጉዳዬ ኮናቴ፣ ሊሊ ማፌላ Ph.D እና ፕሩፌሰር ክሪስቶፈር ኦግቦግቦ ነው።