ኦሮሚያ ክልል ስለተጨፈጨፉ የአማራ ተወላጆች ጉዳይ
ረቡዕ፣ ሰኔ 15 2014ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች እየተፈጸሙ ያሉትን ግድያዎች ገለልተኛ አካል ጣል ገብቶ በማጥናት ይፋ እንዲያወጣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባት (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንገር (ኦፌኮ) ጠየቁ። ባሳለፍነው የሳምንት መጨረሻ ቅዳሜ ዕለት በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞን፣ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ ነዋሪዎች የሆኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ በአብዛኛው የአማራ ብሔር ተወላጆች በታጠቁ ኃይሎች መጨፍጨፋቸው ያስቆጣቸው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድርጊቱን በማውገዝ ሰሞኑን መግለጫ አውጥተዋል። ዛሬ ጉባኤውን ማካሄድ የጀመረው የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በበኩሉ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈጸም የትኛውንም ግድያ በመቃወም መግለጫ አውጥቷል።
ሥዩም ጌቱ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ