1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እየሻከረ የመጣው የኢትዮጵያ እና ምዕራቡ ዓለም ዲፕሎማሲ 

ሐሙስ፣ ነሐሴ 13 2013

በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የሕግ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተመራማሪ ዶ/ር ዓልማው ክፍሌ እንደሚሉት ኢትዮጵያን ለገጠማት የዲፕሎማሲ ፈተና ከጎረቤት እስከ ሌሎች ዓለማት በጠንካራ ዲፕሎማቶች የታገዘ ሥራ መሥራትን የሚጠይቅ ነው።

https://p.dw.com/p/3zB9X
Karte Äthiopien englisch

የውጭ ግንኙነት ይዞታ

ኢትዮጵያ ከምዕራቡ ዓለም ጋር ያላት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እየሻከረ መምጣቱ እየተነገረ ነው። በተለይም በትግራዩ ክልል ከተከፈተው ጦርነት እና አስከትሏል ከተባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ ይዞታው መባባሱ ይታያል። በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የሕግ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተመራማሪ ዶ/ር ዓልማው ክፍሌ እንደሚሉት ኢትዮጵያን ለገጠማት የዲፕሎማሲ ፈተና ከጎረቤት እስከ ሌሎች ዓለማት በጠንካራ ዲፕሎማቶች የታገዘ ሥራ መሥራትን የሚጠይቅ ነው። የውጭ አገር ግንኙነት መርኹም የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ተለዋዋጭነትን ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ መሆን አለበትም ይላሉ።

ስዩም ጌቱ 

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ