እንደ አዲስ በተቀሰቀሰው ግጭት የትግራይ ተወላጆች እየተሰደዱ ነው
በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች እንደ አዲስ በተቀሰቀሰው ግጭት ከቤት ንብረታችው እየተፈናቀሉ ነው። የአከባቢው ከተሞች ፍልሰትን ለመቋቋም እየታገሉ ነው።
ጊዜያዊ መኖሪያ
የ 11 ዓመቷ ታዳጊ አስመራ፤ በሽሬ ከተማ ወደ መጠለያነት በተቀየረ ፀሐዬ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት በር ላይ የአንድ አመት ወንድሟን በረከትን ታቅፋ ቆማለች። የኢትዮጵያ መንግሥት ሕዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይን (ህወሃት) ድል ማድረጉን ከአራት ወራት በፊት ቢገልፅም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች አሁንም ቤታቸውን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል።
ምግብ በመጠበቅ ላይ
የተፈናቀሉ የትግራይ ተወላጆች በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ምግብ ለማግኘት ወረፋ ይዘዋል። እነኝህ ሰዎች በኢትዮጵያ መንግሥት እና በአማፅያኑ መካከል በተደረገ ውጊያ ከመኖሪያ ቤታቸው የወጡ አይደሉም። የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርና የዓይን እማኞች እንደሚገልፁት በአጎራባች አማራና በትግራይ ክልል መካከል ለአስርተ ዓመታት የዘለቀውን የመሬት ውዝግብ የክልሉ ታጣቂዎች በኃይል ለመፍታት እየተሞከሩ በመሆኑ ነው ፡፡
አወዛጋቢ ግዛት
በትግራይ ክልል አዲግራት ከተማ ወደ ኤርትራ መተላለፊያ የሆነች ስልታዊ ጠቀሜታ ያላት ናት። የአማራ ባለሥልጣናት ሕወሓት ሥልጣን ላይ በነበረበት 30 ዓመታት ገደማ፤ ሩብ ያህል የትግራይ መሬት ከአማራ ክልል እንደተወሰደ ይናገራሉ። ሆኖም የትግራይ ባለሥልጣናት አካባቢው የሁለቱም ብሄረሰቦች መኖሪያ መሆኑ፤ እና ድንበሮቹም በሕገ-መንግሥቱ የተቀመጡ ናቸው ይላሉ፡፡
በቅኝት ላይ
የኢትዮጵያ ወታደሮች በአዲግራት አቅራቢያ በጭነት መኪና ጀርባ ላይ ይታያሉ። የአማራ ክልል ይሎች በመጀመሪያ ወደ ትግራይ የገቡት ሕወሓት ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ወደ ግጭት ሲገባ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊቱን ለማገዝ ነበር። ጦርነቱ ጋብ ካለ ወዲህ የአከባቢው ባለሥልጣናት የትግራይ ተወላጆችን አባረዋል በሚል ይወቅሷቸዋል።
መሰረታዊ ፍላጎቶች
ይህ ሰው ፍራሾችን ወደ ሽሬ ፀሐዬ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመውሰድ ተሸክሟል። በቅርቡ የተከሰተው ውዝግብ ቀድሞውኑ አስቸጋሪ የነበረውን የሰብዓዊ ሁኔታ ያባብሰዋል የሚል ስጋት አለ። የሽሬ ሰሜን ምዕራብ ዞን ጊዜያዊ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ አረጋይ በሰጡት አስተያየት ከተማዋ ከቅርብ ጊዜ ስደተኞች በፊት 270 ሺህ ሰዎችን ታስተናግድ የነበረ ሲሆን ከስደተኞች ብዛት የተነሳ ምግብና መጠለያ እየታጣ ነው ብለዋል፡፡
አዲስ የመጡ ስደተኞች
አውቶቡሱ የተፈናቀሉ የትግራይ ተወላጆችን ይዞ ሽሬ ደርሷል። አንዳንዶቹ በተደጋጋሚ የተፈናቀሉ በመሆናቸው በቅርብ ሳምንታት ውስጥ የተሰደዱትን ሰዎች ቁጥር በትክክል ለማጣራት አስቸጋሪ ነው። የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት እንደገለፀው በየቀኑ ወደ 1000 ስደተኞች ወደ ሽሬ ይገባሉ። የኖርዌይ የስደተኞች ምክር ቤት በበኩሉ በመጋቢት ወር በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ከ 140 ሺህ እስከ 185 ሺህ ስደተኞች መግባታቸው ገልጿል ፡፡
ከዩኒቨርሲቲ ግቢነት ወደ መጠለያነት
የተፈናቀሉ የትግራይ ተወላጆችም ወደ ጊዜያዊ መጠለያነት በተለወጠው የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የሽሬ ግቢ እራሳቸውን ለማቆየት ይሞክራሉ።አዳዲስ ስደተኞችን ለማስጠለል በከተማው ውስጥ የተቋቋሙት አራቱ ማዕከሎች ሞልተዋል።አንዳንድ ቤተሰቦች በመማሪያ ክፍሎች ፣ በአዳራሾች እና በግማሽ በተጠናቀቁ ሕንፃዎች ውስጥ ሲጠለሉ ሌሎቹ ደግሞ ታዛ ስር ወይም ሜዳ ላይ ይሰፍራሉ።
የሚወዱትን አቅርቦ መያዝ
በትግራይ ዋና ከተማ መቐለ በሚገኘው በአዲሃ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጊዜያዊ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ ይህቺ ሴት ሕጻን ይዛ ትታያለች። ቤት ንብረታቸውን ጥለው የተሰደዱ ብዙ የትግራይ ተወላጆች በታጣቂዎች ደረሰብን ያሉትን፣ ጥቃት ፣ ዝርፊያ እና ማስፈራሪያ ይገልጻሉ። የተወሰኑት የደረሰባቸው ጉዳት ጠባሳው አለ፡፡
የሚያስተጋባ ግጭት
በአድዋ ከተማ አቅራቢያ አንድ የተቃጠለ ታንክ በትግራይ ክልል ለተፈጠረው ግጭት አስታዋሽ ሆኖ ቆሟል ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቀደም ሲል በትግራይ የጦር ወንጀሎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ያስጠነቀቀ ሲሆን፤ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሌኬን በበኩላቸው የዘር ማፅዳት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን በመግለጽ የአማራ ኃይሎች ከትግራይ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡