1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እንወያይ፤ ኢትዮጵያ ከግጭትና ቀዉስ አዙሪት እንዴት ትዉጣ?

እሑድ፣ ግንቦት 20 2015

በተለያዩ የግጭት ምዕራፍ ውስጥ ገብታ እየተናጠች ያለችው ኢትዮጵያ መውጫዋ ወዴት ይሆን? ምንድን ነዉ ከአንዱ ችግር ወጥተን ወደሌላ ችግር የምንገባበት ምክንያት? መንግሥትን ለመጣል የሚደረግ ትጥቅ ትግል ጊዜዉ ነዉ ወይ? መንግሥትም ሆነ ታጣቂዎች ጦርነት ዉስጥ መግባት ህዝብን ጦርነት ዉስጥ ማስገባት መቼ ነዉ የሚቆመዉ? ከየት ይምጣ ዘላቂው መፍትሄ?

https://p.dw.com/p/4Rtzj
Äthiopische Flagge und Polizist
ምስል DW/J. Jeffrey

ዘላቂው መፍትሄ ከየት ይምጣ?

በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመት የዘለቀዉ እና ሚሊዮኖችን አፈናቅሎ፤ የመቶ ሺህዎችን ህይወት ያጠፋዉ የእርስ በእርስ ጦርነት በፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት ተቋጭቶ የጦር መሳርያ ድምጽን ዝም ማሰኘቱ ለብዞዎች እፎይታን ሰጥቷል። ይሁንና በሃገሪቱ በአንድ በኩል ጦርነት ቆመ፤ ግጭት ቀነሰ፤ መፍትሄ ተገኘ ሲባል፤ ወድያዉ በሌላ አካባቢ ፤ግጭት መቀስቀሱ፤ ብዙዎችን አሳስቧል። በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋና ምዕራብ ሸዋ እንዲሁም በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች፤ የሚካሄደዉ ግጭት እና አለመረጋጋት መፍትሄ ከማግኘት ይልቅ፤ እንደገና ማገርሸቱ እየተዘገበ ነው። አብዛኞች እንደሚሉት በሃገሪቱ ግጭት ግድያ እና መፈናቀል መባባሱ፤ የሃገሪቱን ዉድቀት ብሎም መንግሥት ላይ የሚደርሰዉን ዉግዘት እያፋጠነ ነዉ። ኢትዮጵያ ከአምስት ዓመት ወዲህ የገባችበት የግጭት አዙሪት፤ ማቆምያዉ የት ይሆን? ሕዝቡስ መቼ ነው እፎይ ብሎ ባሻው አከባቢ የሰላም አየር እየተነፈሰ ከአንዱ ጫፍ ወደ ሌላው ጫፍ መንቀሳቀስ የሚችለው? ይህ ቀን አሁንም እሩቅ ይሆን?

በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሃሳባቸዉን ሊሰጡን

አቶ ሙሉጌታ አበበ  የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ )ዋና ፀሐፊ -ከአዲስ አበባ ፤ አቶ ሙላቱ ገመቹ -የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል- ከአዲስ አበባ፤ ዶክተር ደምመላሽ መንግሥቱ በጅማ ዩኒቨርስቲ የግጭት አወጋገድ የባህል ግንኙነትና፣ የህዝብ ዲፕሎማሲ መምህር -ከጅማ  እንዲሁም

ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ የፖለቲካ ሳይንስና የሕግ ምሁር ከጀርመን  ፍራንክፈርት ናቸዉ። በዚህ ዉይይት ላይ የመንግሥት ተወካዮችን ለማሳተፍ ያደረግነዉ ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም።

ተወያዮች የተነጋገሩባቸ ነጥቦች። እርሶስ ምን ይላሉ? ይጻፉልን!

ኢትዮጵያ ከገባችበት የግጭት አዙሪት እንዴት ትዉጣ?

ተወያዮች በተከታዩ ነጥቦች ላይ ተወያይተዋል። እርሶስ ምን ይላሉ? ይጻፉልን!

--በተለያዩ የግጭቶች ምዕራፍ ውስጥ ገብታ እየተናጠች ያለችው ኢትዮጵያ፤ ከነዚህ ግጭቶች መውጫዋ ወዴት ይሆን?

--ምንድን ነዉ ከአንዱ ችግር ወጥተን፤ ወደሌላ ችግር የምንገባበት ምክንያት?

--መንግሥትን ለመጣል የሚደረግ ትጥቅ ትግል ጊዜዉ ነዉ ወይ? አይበቃም ወይ?

--መንግሥትም ሆነ ታጣቂዎች ጦርነት ዉስጥ መግባት፤  ፀጥታን ማወክ፤ ህዝብን ጦርነት ዉስጥ ማስገባት መቼ ነዉ የሚቆመዉ?

-ከየት ይምጣ ዘላቂው መፍትሄ? በመፍትሄው ሂደት ውስጥ ከማን ምን ይጠበቃል? በኃላፊነቱ የአንበሳውን ድርሻ ማን ይውሰድ?

አስተያየታችሁን ጻፉን

ሙሉ ዉይይቱን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ ! አስተያየቶን ይጻፉልን!

አዜብ ታደሰ