እነ እስክንድር እንደታሰሩ ነው
ሰኞ፣ መጋቢት 17 2010ማስታወቂያ
በቅርቡ ከእስር የተፈቱትን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን እና ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌን ጨምሮ 12 ሰዎች ዛሬም እንደታሰሩ ነው። ጎተራ በሚገኘው ፖሊስ መምሪያ የታሰሩት እነዚሁ ሰዎች ለፖሊስ ቃላችንን አንሰጥም ማለታቸውን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘግቧል። ከጋዜጠኞቹ እና ፖለቲከኞቹ በተጨማሪ አክቲቪስት እና ጦማሪዎችም ከታሰሩት ውስጥ ይገኙበታል። ዛሬ ሰዎቹ የታሰሩበት ቦታ የተገኘው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ